በጂንካ ከተማ በቱሪስት ላይ ስርቆት የፈጸሙ ሌቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በ12 ሰዓታት የተጠናቀቀው የ395,000 ብር ስርቆት ፍለጋ!
የጂንካ ከተማ ፖሊስ ባደረገው ያልተቆጠበ ክትትል፣ በአንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ላይ ተፈጽሞ የነበረውን ከፍተኛ የንብረት ስርቆት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ነገሩ እንዲህ ነው ባለፈው እሁድ አጥቢያ ሌሊት 9 ሰዓት አካባቢ፣ ሁለት ግለሰቦች የየዋህ ህጻናትን (የጎዳና ተዳዳሪዎችን) "ገንዘብ እንሰጣችኋለን" በሚል በማባበልና በመስኮት በማስገባት፣ ተኝቶ በነበረ የውጭ ሀገር ዜጋ ላይ፦
* አንድ iPhone 13 Pro Max ስልክ እና
* አንድ ላፕቶፕ (በአጠቃላይ ግምታቸው 395,000 ብር) እንዲሰረቅ አድርገዋል።
የጂንካ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ካሌብ ከብትይመር እንደገለጹት፣ ወንጀሉ እንደተፈጸመ ማህበረሰቡ በሰጠው ፈጣን ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ብርቱ ክትትል ጀምሯል። ሌቦቹ ለማምለጥ ቢሞክሩም በ12 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ንብረታቸው የተመለሰላቸው ቱሪስት፣ ፖሊስ ላሳየው ብቃትና ፍጥነት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። "በአጭር ጊዜ ውስጥ ስልኬንና ላፕቶፔን አግኝቼ ሌቦቹንም በቁጥጥር ስር በማዋላቸው የጂንካ ፖሊስ በእርግጥም ሊመሰገን ይገባዋል" ሲሉ በደስታ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋ/ሳጅን ሙሴ ወልደ፣ ህዝቡ ፀጉረ-ለወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት አሁንም ጥቆማ መስጠቱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
Via ጂንካ ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

4 months ago