Logo
Getu Temesgen
"ለኔ ኤፌ ካፕም ሻምፒየንስ ሊግም ያው ነው" — አርነ ስሎት

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ አርነ ስሎት ስለ እንግሊዝ ኤፌ ካፕ ያላቸውን ከፍተኛ ግምት ገልጸዋል። አሰልጣኙ የውድድሩን ፈታኝነት ሲገልጹ የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፡-

የውድድሩ ጥንካሬ፦ እንደ ስሎት አገላለጽ፣ የኤፌ ካፕ ውድድር ከሻምፒየንስ ሊግ ጋር የሚመጣጠን ከባድ ፈተና የሚታይበት መድረክ ነው።

ልዩነቱ፦ "በውድድሩ ላይ እነ ፒኤስጂ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና ባየር ሙኒክ አለመኖራቸው ብቻ ነው ከሻምፒየንስ ሊግ የሚለየው" ሲሉ በጨዋታ መልክ የውድድሩን ደረጃ አግንነዋል።

የስቦዝላይ ብቃት፦ አሰልጣኙ ስለ ዶሚኒክ ስቦዝላይ ሲናገሩም "በዚህ የውድድር ዓመት በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው" ሲሉ ለሃንጋሪያዊው አማካይ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #ሊቨርፑል #አርነስሎት #ስፖርት #ኤፌካፕ #ethiopia # #lfc #arneslot #facup #szoboszlai

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.