39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ
#ethiopia | በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የሀገራት መሪዎች የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በተመለከተ ጠንካራ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪነት ያላትን ድርሻ በተመለከተ ደፋር ጥሪ አቅርበዋል። "ይህ 2026 እንጂ 1946 አይደለም" ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አፍሪካውያን ለችግሮቻቸው አፍሪካዊ መፍትሔ የመስጠት አቅም እንዳላቸው ጠቅሰው፤ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለጋራ ብልጽግና ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የአውሮፓ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በአፍሪካ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመጥቀስ፣ ጣሊያን በአህጉራቱ መካከል እንደ ድልድይ ሆና እንደምታገለግልና ስደትን ለመቀነስ የሥራ ዕድል መፈጠር እንዳለበት አሳስበዋል።
የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሙስጠፋ አፍሪካ ለፍልስጤም ነፃነትና ሉዓላዊነት ለምታሳየው ጽኑ አጋርነት ምስጋና አቅርበው፣ አህጉሪቱ ለሰላም የምታደርገውን ድጋፍ እንድታጠናክር ጠይቀዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ "ውሃ እና ንጽህና አጠባበቅ” " በሚል መሪ ቃል፤ የመሰረተ ልማት ትስስር፣ የነፃ ንግድ ቀጠና እና የወጣቶች የፈጠራ ክህሎት ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ
ጌትነት ተመስገን
#au #africaunion #ethiopia #addisababa #globalsouth #agenda2063

4 months ago