የጉበት ህመም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ የንቃት መቀነስ እና የአዕምሮ መዛባትን ያስከትላል ተባለ
ጉበት በሰውነታችን የሆድ እቃ ውስጥ በቀኝ በኩል የሚገኝ የአካል ክፍል ነው ።ለሴቶች ከቀኝ ጡት ወረድ ብሎ ለወንዶች ደግሞ ከታችኛው የጎድን አጥንት ስር የሚገኝ ጠቃሚ የሰውነት ክፍል ነው ። ተግባራቱም የምንመገባቸውን ካርቦ ሀይድሬት ፣ስብ እና ፕሮቲን እንዲብላሉ እና እንዲዋሃዱ የሚያደርግ መሆኑን በሀባሪ ሜዲካል ፕላዛ እና ሜዲካል ሴንተር የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ኤዶሚያስ አደምሰገድ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
እንደ ዶ/ር ኤዶሚያስ ገለፃ ጉበት የምንመገበውን ስብ እንዲዋሀድ እንዲፈጭ የሚያደርገውን ሀሞት ማምረት እና የተለያዩ ኬሚካሎች፣መድሃኒቶች እና መጠጦችን በማጣራት ከሰውነት እንዲወገዱ የሚያደርግ ብሎም ሌሎችም በርካታ ተግባራት የሚያከናውን የሰውነት ክፍል ነው።
ይሁን እና ጉበት በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚጎዳ እና የሚያሳየው ምልክትም እንደ ጉዳቱ ደረጃ የተለያየ ሲሆን መጀመሪያ አካባቢ ግልፅ ያልሆኑ ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ። በአንዳንድ ሰዎች ላይ ድካም የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የክብደት መቀነስ ፣የማቅለሽለሽ እና በቀኝ የሆድ ክፍል ላይ ህመም መኖር ሊያስከትል ይችላል።ህመሙ ግን እየከፋ በሚመጣበት ጊዜ የሰውነት ቆዳ ማሳከክ ፣ የአይን ቢጫ መሆን እና የሽንት መጥቆር ሊያስከትል እንደሚችል ገልፀዋል።
በተጨማሪም ህመሙ እየባሰ ሲሄድ የንቃት መቀነስ እና የአዕምሮ መዛባት ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል ። እንዲሁም ብዙ አይነት የጉበት ህመም መኖሩን አንስተዋል ።ከነዚህም ውስጥ ከቫይረስ ጋር የሚመጡ ኢንፌክሽኖች ፣በአልኮል መጠጥ ፣ ከውፍረት እና ከስብ ክምችት ፣ በዘር የሚተላለፉ እና ሌሎችም የጉበት ህመሞች መኖራቸውን ገልፀዋል።የአልኮል መጠጥን በመተው ፣ውፍረትን በመቀነስ እና ክትባት በመውሰድ የጉበት ህመምን መከላከል እንደሚቻልም ዶ/ር ኤዶሚያስ አለምሰገድ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
seledadotio

4 months ago