ተከዳው በማለት በምስራቅ ሐረርጌ መንታ ልጆቿ የገደለችው ኡርጂ መሐመድ በ23 ዓመት እስራት ተቀጣች
"ባደረገችው ነገር አልተቆጨችም፤ ይልቁንም 'አባት የሌላቸውን ልጆች ማሳደግ ከባድ ስለሆነ ነው የገደልኳቸው' ስትል ለፖሊስ ቃሏን ሰጥታለች።"
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በማያ ከተማ አስተዳደር አወዳይ ክፍለ ከተማ ጫልቱ ቀበሌ ውስጥ የተፈጸመው ይሄው አሰቃቂ ድርጊት፣ መላውን ነዋሪ አስደንግጧል። ጉዳዩ እንዲህ ነው፦
የክህደቱ መጀመሪያ፦ ወጣት ኡርጂ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ እያለች መንታ ልጆችን ትጸንሳለች። ይሁን እንጂ አባትየው እርግዝናውን እንደሰማ ጥሏት ይሰወራል።
አሰቃቂው እርምጃ፦ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ወንድና ሴት መንታ ልጆችን በሰላም ብትገላገልም፣ ከቤት እንደገባች ግን በጭካኔ አፍና በመግደል በጓሮዋ ቀብራቸዋለች።
ሚስጥሩን ያጋለጠው ድንጋይ፦ ድርጊቱን የጠረጠረው ታናሽ ወንድሟ፣ በጓሮ የተቆለለ አፈርና በላዩ ላይ የተቀመጡ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችን ተመልክቶ ለሀገር ሽማግሌዎች ጥቆማ ይሰጣል።
የህግ ውሳኔ፦ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ አስከሬኖቹ የወጡ ሲሆን፣ የማያ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በፈጸመችው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል የ23 ዓመት ፅኑ እስራት በይኖባታል።

4 months ago