በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ ያለመ "የሂሳብ ኣያያዝ ቴክኒሺያን የሥልጠና ፕሮግራም" ይፋ ሆነ።
በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከሆኑ የኦዲትና የሙያ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንዱ የሆነው ኤች.ኤስ.ቲ (HST)፤ በሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ የታየውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ ያለመ "የሂሳብ ኣያያዝ ቴክኒሺያን የሥልጠና ፕሮግራም" (HST-ATTP) በይፋ አብስሯል።
የኤች.ኤስ.ቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ግዛው ስልጠናው በስሩ በሚገኘው የክህሎት አካዳሚ (HST Skill Academy) አማካኝነት የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው በዋናነትም በግል ዘርፉ፣ በመንግሥት ተቋማትና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) ውስጥ የሚስተዋለውን የብቁ የፋይናንስ ባለሙያዎች ፍላጎት ለማርካት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃን ከሀገር በቀል ተሞክሮ ጋር ማጣመሩ፣ ስልጠናው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው የኤ.ሲ.ሲ.ኤ (ACCA) የሂሳብ ኣያያዝ ቴክኒሺያን ስርአተ-ትምህርት ላይ ተመስርቶ እና ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተጣጥሞ የቀረበ መሆኑ ከቀደሙት የስልጠና አይነቶች ለየት እንደሚደርጉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።
ስልጠናው ዘመናዊውን የኤች.ኤስ.ቲ የኢ-ለርኒንግ ፕላትፎርም (learn.hst-et.com) በመጠቀም ሰልጣኞች በማንኛውም ቦታና ጊዜ እንዲከታተሉት ያስችላልም ተብሏል።
ተግባር ተኮር ዝግጅት ንድፈ-ሃሳብን (Theory) ብቻ ሳይሆን ሰልጣኞች በቀጥታ ወደ ሥራ ገበታ ሲሰማሩ የሚያስፈልጋቸውን የሙያ ስነ-ምግባርና ተግባራዊ ክህሎት እንዲጨብጡ ተደርጎ የተቀረጸ ነው።
ኤች.ኤስ.ቲ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኦዲት፣ በታክስና በስትራቴጂክ ማማከር ዘርፍ የገነባውን ስም በመጠቀም፣ ይህ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ተገልጿል።
በተለይም በዘርፉ አዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠርና የዜጎችን የመወዳደር አቅም ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል።
ስለ ስልጠናው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚፈልጉ አካላት በተቋሙ ድረ-ገጽ www.hst-et.com ወይም በስልጠና ፖርታሉ learn.hst-et.com መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

8 months ago