Logo
FIDEL POST NEWS
በልመና ሚሊየነር የሆነው ህንዳዊ

👉በልመና ብቻ በወር 140 ሺ ብር ድረስ ያገኛል

​አካል ጉዳተኛ በመምሰል ለዓመታት ሲለምን የነበረው የ50 ዓመቱ ህንዳዊ ባራት ጄን በዓለም ላይ "ሀብታሙ ለማኝ" ተብሎ ተፈርጇል።

ይህ ሰው በሙምባይ ጎዳናዎች ላይ በዊልቸር እና በቆርቆሮ እየተንቀሳቀሰ የሰዎችን አዘኔታ በማግኘት የገነባው የሀብት ግዛት ለብዙዎች አስገራሚ ሆኗል።

በምርመራ የተደረሰባቸው አስገራሚ ሀብቶቹ፦

​ወርሃዊ ገቢ፦ በልመና ብቻ በወር እስከ $900 (75,000 የህንድ ሩፒ) ያገኛል።

​የሪል ስቴት ባለቤትነት፦ በሙምባይ ከተማ ባለ 3 ፎቅ ህንፃ እና ሁለት ተጨማሪ አፓርታማዎች አሉት። የቤቶቹ ግምት ከ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ይገመታል።

​የንግድ ስራ፦ ለነጋዴዎች በወለድ ብድር ይሰጣል፤ እንዲሁም ሁለት የንግድ ሱቆችን ለኪራይ ሰጥቶ በወር 30,000 ሩፒ ተጨማሪ ገቢ ያገኛል።

​ቅንጡ ህይወት፦ ለራሱ የግል መኪና እና ሹፌር ያለው ሲሆን፣ ልጆቹንም በታዋቂ የግል ትምህርት ቤቶች (Convent Schools) ያስተምራል።

​⚠️ ለምን አሁንም ይለምናል?

የህንድ ፖሊሶች እና ቤተሰቦቹ ስራውን እንዲያቆም በተደጋጋሚ ቢመክሩትም፣ ባራት ግን "ልመና የህይወቴ አካል ነው" በማለት አሁንም በቀን ከ10 እስከ 12 ሰዓታት በጎዳናዎች ላይ ይታያል።

​"ሰዎች የሚሰጡት ሳንቲም ተከማችቶ ፎቅ እንደሚሰራ ትልቅ ማሳያ ነው፤ ነገር ግን ይሄ ድርጊት በእውነት ለሚቸገሩ ሰዎች የሚሰጠውን እረዳታ ጥርጣሬ ውስጥ ጥሎታል" ሲሉ ብዙዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

​የእርስዎስ አስተያየት ምንድነው? እንዲህ አይነት ሰዎች በእውነት የሚረዱትን አያሰናክሉም?
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.