Logo
FIDEL POST NEWS
የአቢሲኒያ ባንክ አዲስ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ አደረገ!

​የአቢሲኒያ ባንክ ነባር ባለአክሲዮኖች በሙሉ!
​የአቢሲኒያ ባንክ (Bank of Abyssinia S.C) ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባገኘው ፈቃድ መሰረት ለነባር ባለአክሲዮኖች 3,125,000 አዳዲስ ተራ አክሲዮኖችን ለሽያጭ ማቅረቡን በደስታ ያበስራል።

​ቁልፍ መረጃዎች፡

​💰 የአንድ አክሲዮን ዋጋ፦ 1,600 ብር

​📅 የሽያጭ ጊዜ፦ ከጥር 22 ቀን 2018 እስከ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

​⚖️ የአከፋፈል ሁኔታ፦ አክሲዮኖቹ የሚከፋፈሉት እንደ ነባር የባለቤትነት ድርሻ (Pro rata basis) ይሆናል።

​ለመግዛት ምን ያስፈልጋል?
ባለአክሲዮኖች በካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፈቃድ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ደላሎች (Investment Brokers) ዘንድ በመቅረብ የንግድ አካውንት መክፈትና የግዢ ትዕዛዝ መስጠት ይኖርባቸዋል።

​አስፈላጊ ሰነዶች፦
​ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ ቁጥር)
​የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN
​የኢሜል አድራሻ (Email)
​በወኪል ለሚፈጽሙ ደግሞ ሕጋዊ የውክልና ስልጣን ማስረጃ

​ማሳሰቢያ፦ ኢንቨስት ከማድረግዎ በፊት የባንኩን "Prospectus" (መረጃ መግለጫ) ሙሉ በሙሉ እንዲያነቡና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የፋይናንስ ባለሙያዎችን እንዲያማክሩ ይመከራል።

​ለበለጠ መረጃ፦
📍 ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በሚከተሉት ስልኮች ይደውሉ፡
📞 +251-115-526314 | 0974-506535 | 0911-373294 | 0937-439882
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.