Logo
YenetaTube
አባቱ ግብጻዊ ክርስቲያን ሲሆን ጣዖት አምላኪዋ ሶርያዊት እናቱ ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር፡፡

ልጃቸው በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቃ ከሚባሉት ሰማዕታት አንዱ ማር ቴዎድሮስ በ3ኛው መቶ ክ.ዘ በሶርያ ተወለደ፡፡ ሲወለድም አባት ክርስትና ለማስነሳት ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ፡፡

ሚስት በባለስልጣን ወገኖቿ ልጁን ቀምታ አሳደደችው፡፡ አባት ሸሽቶ ወደ ግብጽ ቢሔድም ስለ ልጁ ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይጸልይ ያለቅስም ነበር፡፡ ልመናውን ተሰምቶለትም ማር ቴዎድሮስ በወጣትነቱ በራሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ፣ ተጠመቀም፡፡ ለጾም፣ ለጸሎትና ለምጽዋት ተጋ፡፡ በድንግልና ጸንቶ ለመኖርም የታመነ ሆነ፡፡

ገና በ20 ዓመቱ ነገሥታቱም የአንጾኪያ ጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት፡፡ ማር ቅዱስ ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም፡፡ ከፋርስ ሰዎች ጋር በተደረገ ጦርነት የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ቢሰጠው ብቻውን አሸንፏቸዋል፡፡ አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ሲገባ 24 ክንድ የሚረዝም ዘንዶ ሲመለክና ክርስቲያኖችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርቧቸው፣ ዘንዶውን በጦር ገደለው፡፡ አባቱን አፈላልጎ አግኝቶ ሕይወቱ እስኪያልፍ አብሮት ቆይቶ ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ክርስትና ጠፍቶ ጣዖት ሲመለክ፣ ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ፡፡

በንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ ንጉሡም በጽኑ መከራ ሲያሰቃየው በእግዚአብሔር ኃይል ጸና፣ ታገሠም፡፡ ጌታችን በግርማ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቶት ዐረገ፡፡ በመጨረሻም አንገቱን ተሰይፎም የክብር አክሊል ተቀብሏል፡፡ በተጋድሎውን ያመኑ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል፡፡ ስለክርስቶስ ፍቅር ዓለምንና ክብራቸውን የተዉ ገዳማውያንም የጸሎታቸው በረከት ለብዙዎች ይተርፋል፣ የነፍስ ምህረት የስጋ ድህነት ያሰጣልና ገዳማቸውን እናግዝ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.