Logo
Getu Temesgen
ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለሀገር ባበረከቱት አስተዋጽኦ ተሸለሙ! 🇪🇹
#ethiopia | ​"የማርበርግ ቫይረስን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ላደረጉት አመራር እውቅና ተሰጠ"

​የጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ ሀገር አቀፍ የጤና ግብረ ኃይልን በመምራት ድንገተኛ የጤና አደጋ ክስተቶችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ላሳዩት ከፍተኛ ቁርጠኝነት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

​በተለይም የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus) ከኢትዮጵያ እንዲወገድ ባደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ እጅ ሽልማቱን ተቀብለዋል።

​ይህ ሽልማት የጤናው ዘርፍ ለህብረተሰቡ ደህንነት እየከፈለ ላለው ዋጋ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።

​ክብርት ሚኒስትር ላደረጉት አስተዋጽኦ እናመሰግናለን! 👏🏥

​#drmekdesdaba #ministryofhealth #award #publichealth #ethiopia #marburgfree #moh

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.