Logo
FIDEL POST NEWS
በጀርመን በአስከሬኖች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ፈጸሟል የተባለው ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

​በጀርመን ቢንደ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ፣ የሟቾችን አስከሬን በጾታዊ ግንኙነት ሲያረክስ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።
​
​ተጠርጣሪው የ39 ዓመት ግለሰብ በሆስፒታሉ የፓቶሎጂ ክፍል ውስጥ በጽዳት እና ጥገና ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ሲሆን፣ ይህንኑ አጋጣሚ በመጠቀም በሟቾች ላይ ጥቃት ሲፈጽም እንደነበር ተደርሶበታል ሲሉ ሰሞኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ​ድርጊቱ የተፈጸመው በሰኔ እና በታህሳስ ወር 2025 (እ.ኤ.አ) ውስጥ ሲሆን ​ጥቃቱ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት አስከሬን ላይ ተፈጽሟል ተብሏል።

​የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች የአስከሬኖቹን አቀማመጥ እና በቦታው ላይ የተገኙ አጠራጣሪ ምልክቶችን ተከትሎ ለህግ አካላት ጥቆማ ሰጥተዋል።

​ፖሊስ በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ባደረገው ፍተሻ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን እና ማስረጃዎችን የያዘ ሲሆን፣ ግለሰቡም ለDNA ምርመራ የሚሆን የምራቅ ናሙና እንዲሰጥ ተደርጓል።
​
​በጀርመን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት፣ ድርጊቱ "የሟቾችን ሰላም እና ክብር ማናጋት" በሚል ወንጀል የሚመደብ ሲሆን፣ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ሊቀጣ ይችላል።
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.