እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡
በግብጽ በስደቷ፣ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡
ከሙታን ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ለተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡
ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ጡዋፍ ዘቢብ መባእ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእርሷና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሚሰይሙትን ሁሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡
ጌታችንም በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈ፣ “ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ የካቲት 16 ቀን ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ እኛም ማደሪያው ትሆን ዘንድ ከመረጣት ከእመቤታችን ጋር ዕለቱን በየወሩ በ16ኛው ቀን በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን፡፡ ይህን ቃል ኪዳኗን ያመኑ፣ በእናትነት ፍቅሯ ከምልጃዋ በረከት የተካፈሉ ገዳማውያን ሌሊትና ቀን ቅድስት ሆይ ለምኝንልን ይሏታል፡፡ የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር ሳይበግራቸው በጸሎተው ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የእመቤታችን በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

4 months ago