Logo
Getu Temesgen
⚖️ በሽምግልና ብቻ ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ዳነ!

* ​"ፍርድ ቤት መር አስማሚነት፡ ጊዜንና ገንዘብን የሚቆጥብ ዘመናዊ አሰራር"

​የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በተጠናቀቀው ግማሽ በጀት ዓመት ተግባራዊ ያደረገው "የፍርድ ቤት መር አስማሚነት" (Court-Annexed Mediation) አሰራር አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አስታውቋል።

​የግማሽ ዓመቱ አፈጻጸም በቁጥር:

✅ የተቋጩ መዛግብት:
በ13 ምድብ ችሎቶች 610 መዛግብት ወደ ክርክር ከመግባታቸው በፊት በስምምነት ተዘግተዋል።

💰 የዳነ ወጪ:
በእነዚህ መዛግብት ውስጥ የነበረው የክርክር መጠን 135 ሚሊዮን 374 ሺህ ብር በላይ ሲሆን፤ ጉዳዩ በስምምነት መለቀቁ ይህን ያህል ገንዘብ እና ጊዜ ከብክነት አድኗል።

​የአሰራሩ ፋይዳ:
ይህ አሰራር ተከራካሪዎች በፍርድ ቤት የሚፈጁትን ጊዜ እና የሚያወጡትን ወጪ ከመቀነስ ባለፈ፤ ለሀገር ኢኮኖሚም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

​ምንም እንኳን የአስማሚዎች ቁጥር ማነስ እና የተከራካሪዎች በውል ያለመቅረብ ክፍተቶች ቢኖሩም፤ አፈጻጸሙ እጅግ ተስፋ ሰጪ መሆኑ ተገልጿል።

​ሰላም እና ስምምነት ለሁሉም ይበጃል! 🤝

የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት

​#federalcourt #mediation #justicesystem #ethiopia #costsaving #legalreforms

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.