Logo
FIDEL POST NEWS
በስፔን የእስቴፈን ሆኪንግ" ሰልፍ!

​በስፔን ካዲዝ (Cadiz) ከተማ በሚካሄደው አመታዊ የካርኒቫል በዓል ላይ፣ በርካታ ሰዎች ዝነኛውን የፊዚክስ ሊቅ እስቴፈን ሆኪንግን በመምሰል በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ደመቅ ያለ ሰልፍ አድርገዋል።

​በዝግጅቱ ላይ፦
​ተሳታፊዎቹ ልክ እንደ ሳይንቲስቱ በዊልቸር በመሆን እና የእሱን የንግግር ድምፅ (Robotic voice) በመምሰል ሲዘፍኑ ተስተውለዋል።

​"Una chirigota en teoría" የተሰኘው ይሄ የኪነ-ጥበብ ቡድን፣ ዝግጅቱን ለታላቁ ሳይንቲስት መታሰቢያ እንዲሆን ያዘጋጀው መሆኑን ገልጿል።

​መልካም ተግባር፦
ይህ ዝግጅት ለፈገግታ ብቻ ሳይሆን ለበጎ አድራጎትም ጭምር ነው! ለዝግጅቱ አገልግሎት ላይ የዋሉት የኤሌክትሪክ ዊልቸሮች በሙሉ፣ ሆኪንግ ሲሰቃይበት ለነበረው የ ALS (Amyotrophic Lateral Sclerosis) በሽታ ተጠቂዎች በዕርዳታ እንዲሰጡ ተወስኗል።

​ብዙዎች የቡድኑን ፈጠራ እና የበጎ አድራጎት ሃሳብ አድንቀውታል።
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.