Logo
SeledaPost
አሜሪካ የቁም ከብት፣ የ1 ቀን ጫጩቶችንና የሚፈለፈሉ እንቁላሎችን ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ ነው።

አሜሪካ የቁም የከብት እንስሳትን፣ አንድ ቀን የሞላቸውን ጫጩቶች እና የሚፈለፈል እንቁላል ለኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችላትን ፈቃድ ማግኘቷን አስታወቀች።

አሜሪካ ከዚህ ቀደም ወደ ኢትዮጵያ የወንድ ከብት የዘር ፈሳሽና የጎለበተ የከብት ፅንስ( embryo) ለመላክ ፈቃድ እንደነበራት ገልፃለች።

ኢትዮጵያ 70 ሚሊየን ከብት፣ 43 ሚሊየን በግ፣ 53 ሚሊየን ፍየል፣ 8 ሚሊየን ግመልና 57 ሚሊየን ዶሮ ያላት ሲሆን ዘርፉ ከግብርናው ጥቅል ምርት 45 በመቶውን ይይዛል።

አሜሪካ አዲሱ የገበያ አማራጭ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ታህሳስ 16፣ 2025 ላይ ማጽደቋን ይገልጻል።

seledadotio
seledadotio
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.