"ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ስለሚኖር የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት ሰብስቡ" - የሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
#ethiopia | በአንዳንድ የመኸር አብቃይ የሀገሪቱ ክፍሎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል፣ አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን በአፋጣኝ እንዲሰበስቡ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።
ኢንስቲትዩቱ እንደገለጸው እስከ ጥር ወር መጀመሪያ ቀናት ድረስ በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች ደረቃማ አየር ቢጠበቅም፣ በታኅሣሥ መጨረሻና በጥር መጀመሪያ ቀናት ግን በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ አነስተኛ መጠን ያለውና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊኖር ይችላል።
ዝናብ ሊኖርባቸው የሚችሉ አካባቢዎች፦🔎
ኢንስቲትዩቱ ዝናቡ ሊኖርባቸው ይችላል ያላቸውና ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች የሚከተሉት ናቸው፦
* አማራ ክልል፦ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ ባሕር ዳር ዙሪያ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ።
* ትግራይ ክልል፦ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ትግራይ ዞኖች።
* ኦሮሚያ ክልል፦ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ።
* ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፦ የክልሉ የተለያዩ
ዞኖች።
📌የተሰጠ ምክረ-ሀሳብ፦
⛈ ወቅቱን ያልጠበቀው ዝናብ በሰብል ምርት ጥራትና መጠን ላይ ጉዳት እንዳያደርስ፣ አርሶ አደሩ የሚኖሩትን ደረቃማ ቀናት በመጠቀም ምርቱን በፍጥነት ሰብስቦ ለጥንቃቄ ወደሚሆን ስፍራ እንዲያስገባ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #weatheralert #agriculture #harvest2018 #meteorology #farmersadvice #climatewatch

6 months ago