Logo
Getu Temesgen
ከሞት ወደ ህይወት
#ethiopia | በደም ካንሰር በሽታ የዳነችው አሊሳ ለብዙዎች ተስፋ ሆናለች።

ሕክምናው የሳይንስ ልብ ወለድ ይመስላል።

በፍጥነት እየተስፋፋ ያለ እና ሕክምና የሌለው የደም ካንሰር ከያዛቸው ሕሙማን የተወሰኑት ላይ ለውጥ እንደታየ ዶክተሮች ገልጸዋል።

ሕክምናው የሚሰጠው በነጭ የደም ሕዋሳት ላይ የዘረ መል ምህንድስና በማድረግ ነው።

ነጭ የደም ሕዋሳት የዘረ መል ምህንድስና ከተደረገላቸው በኋላ ካንሰርን መዋጋት የሚችሉ ይሆናሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሕክምናው ስለተሰጣት ሰው ቢቢሲ በአውሮፓውኑ 2022 ዘገባ ሠርቶ ነበር።

አሊሳ ታሚሊ ከሕመሙ ከዳነች በኋላ የካንሰር ተመራማሪ ሳይንቲስት ለመሆን ቆርጣ ተነስታለች።

በዚህ የደም ካንሰር ዓይነት
(T-cell acute lymphoblastic leukaemia) ለተያዙ ስምንት ሕጻናት እና ሁለት አዋቂዎች ሕክምናው ተሰጥቷል።

ከታካሚዎቹ 64 በመቶ የሚሆኑት አገግመዋል።

ከሦስት ዓመት በፊት የተካሄደው ታሪክ ለዋጭ ሕክምና የቀድሞውን የሰውነቷን በሽታ የመከላከል አቅም በአዲስ ለውጧል።

ለአራት ወራት ሆስፒታል ተኝታ ስትታከም ኢንፌክሽን እንዳይዛት በሚል ወንድሟ አይጠይቃትም ነበር።

አሁን ካንሰሩ በሰውነቷ ውስጥ እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።

በየዓመቱ ጤናዋን ለመከታተል ሆስፒታል ትሄዳለች።

አሊሳ መኪና መንዳት እየተማረች ነው።

በበጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ላይም ተሰማርታለች።

"ባዮሜዲካል ሳይንስ ውስጥ እንደ ጀማሪ ባለሙያ መሥራት እፈልጋለሁ።

አንድ ቀን የደም ካንሰር ምርምር ውስጥ እንደምገባ ተስፋ አደርጋለሁ" ትላለች።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

​#bbc

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.