Logo
SeledaPost
ኢትዮ ቴሌኮም በአገልግሎቶቹ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ወቅታዊውን የሀገሪቱን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ እና በአማካይ የ23 በመቶ የዋጋ ማስተካከያ ማድረጉን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። ተቋሙ ማሻሻያውን ያደረገው የአገልግሎት ጥራትን በዘላቂነት ለማስጠበቅና የቴክኖሎጂ አቅሙን ለማሳደግ መሆኑን ገልጿል።

የታሪፍ ማሻሻያው ዋና ዋና ነጥቦች፦

✅ የ20% የቴሌብር ቅናሽ ስጦታ፦ በቴሌብር (telebirr) ጥቅል ለሚገዙ ደንበኞች ቀደም ሲል የነበረው የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ እንዲል ተደርጓል።

✅ ዋጋቸው ያልተቀየሩ ጥቅሎች፦ በርካታ ደንበኞች ዘንድ ተመራጭ የሆኑ 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።

✅ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ደንበኞች፦ ዲጂታል አካታችነትን ለማረጋገጥ ሲባል የ1 ብር፣ የ2 ብር፣ የ5 ብር እና የ1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት ዋጋ እንዲቀጥሉ ተወስኗል።

እንደ ተቋሙ መግለጫ ከሆነ፤ በዘርፉ ላይ የታየውን የወጪ ጫና መቋቋም፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ማፋጠን እና መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት የታሪፍ ማስተካከያው የግድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም የዋጋ ጭማሪው ተመጣጣኝ እንዲሆን ጥረት ማድረጉን የገለፀ ሲሆን፣ ይህም ደንበኞች በዲጂታል አገልግሎቶች ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማስቀጠል ያለመ መሆኑን ጠቁሟል።

Via Ethio Telecom

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.