የቅዱስ ገብርኤል በዓል እየተከበረ ነው
#ethiopia | የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በድምቀት እየተከበረ ነው።
በክብረ በዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ የምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ አህጉረ ስብከት ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፣ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የጉጂ፣የምዕራብ ጉጂ ቦረና ሊበን ዞኖችና የምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ፣አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የጠቅላይ ቤተክህነት ፣ የተለያዩ ሀገረ ስብከት የመምሪያ ኃላፊዎች እና በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ከትናንት ዋዜማ ጀምሮ በተለያዩ መንፈሳዊ መርሐግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
በየአመቱ ታህሳስ 19 ቀን የሚከበረው በዓል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተገለጸው አናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) የተባሉ ታዳጊዎች "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል" ያሉበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሣት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው።

6 months ago