በአማራ ክልል የኬላዎች መነሳት አሁንም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዳልሆነ ተገለጸ
#ethiopia | የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ኬላዎች እንዲነሱና ያልተገቡ የገንዘብ ስብስባዎች እንዲቆሙ ደብዳቤ ቢጽፍም፣ አሁንም ድረስ ያልተነሱና ለአሽከርካሪዎች እንግልት የሆኑ ኬላዎች መኖራቸውን ተገልጿል።
የጣና ከባድ መኪና አሽከሪካሪዎች ማህበር ዋና ጸሃፊ አቶ ሰጡ ብርሃን እንደገለጹት፥ቀደም ሲል የገቢዎች ቢሮ በወጣው መመሪያ መሰረት የተነሱ ኬላዎች ቢኖሩም አሁንም በየቦታው የቀሩና ለአሽከርካሪዎች ከፍተኛ የገንዘብ ጫና የሚፈጥሩ ኬላዎች መኖራቸዉን አንስተዋል።
በተለይም በየ3መቶ ኪሎሜትሩ እስከ 12 የሚደርሱ ኬላዎች መኖራቸውንና በእነዚህ ኬላዎች ላይ የመንገድ ፈንድ፣ የልማት (አልማ)፣ የስፖርት እና የቀይ መስቀል በሚሉ ስሞች የተለያዩ ክፍያዎች እንደሚጠየቁ ገልፀዋል።
ደብዳቤ መጻፉ ብቻውን በቂ አይደለም የሚሉት አቶ ሰጡ፥ የክልሉ መንግስት መሬት ላይ ወርዶ አፈጻጸሙን ሊከታተል ይገባል ደብዳቤው ሁልጊዜም ይጻፋል፣ ነገር ግን ተግባራዊ የሚያደርገው አካል የለም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
በአንዳንድ ቦታዎች አሽከርካሪዎች ክፍያ አንከፍልም ሲሉ ታርጋቸውን እስከመፈታትና መንገድ እስከመዘጋጋት የሚደርስ እንግልት እንደሚደርስባቸውም ተናግረዋል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

10 months ago