Logo
YenetaTube
ሼፍ መክብብ የ ማይ -ክሽን ብራን አንባሳደር ተደረገ “

የ20 ዓመታት ልፋቴን ውጤት ዛሬ አይቼአለሁ" ሼፍ መክብብ ዘውዴ

በኢ.ቢ.ኤስ. በሚተላለፈው "ምርጡ ገበታ" የተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በዳኝነት የሚታወቀው ሼፍ መክብብ ዘውዴ፤ የ"ማይ-ክሽን" ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ፡፡ ሼፍ መክብብ ከብራንድ አምባሳደርነቱ ሹመት በኋላ እንደተናገረው፣ ከ"ማይ-ክሽን" ጋር በርካታ ስራዎችን ለመስራት አቅዷል።

በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነው መርሐ ግብር ላይ የ"ማይ-ክሽን" አምራች የሆየው ሎንግሪቨር አግሮ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ሃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች ተገኝተዋል። የሎንግሪቨር አግሮ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ሃላፊዎች፣ ቅመማቅመም ተኮር ከሆነው የማምረት ዘርፍ ባለፈ፣ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

አያይዘውም፣ ገበያ ላይ ያሉ ምርቶችን በድጋሚ ከማቅረብ ይልቅ "አዳዲስና በፈጠራ ይዘት የተሞሉ" ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውንና በተለይ በምግብና ቅመማቅመም ዘርፍ ውስጥ ኩባንያቸው "የራሱን አሻራ" ለማሳረፍ የተለያዩ ሙከራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል። "ኢትዮጵያ ዋነኛ የምርትና የገበያ ማዕከላችን ናት" ያሉት ሃላፊዎቹ፣ የኩባንያቸውን ምርቶች ወደ አሜሪካና ብሪታኒያ እየላኩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዛሬው ዕለት ከሼፍ መክብብ ጋር ለመስራት የአጋርነት ስምምነት ለመፈራረም በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት ሃላፊዎቹ፣ የኩባንያቸውን ስራ ለማስፋት ሼፍ መክብብ ጉልሕ አስተዋጽዖ ሊያበረክት "ይችላል" የሚል ተስፋ እንዳላቸው አልሸሸጉም።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.