Logo
SeledaPost
የእርሻ ማሳ ውስጥ የገባ ዝሆን የ76 ዓመቱን አዛውንት ሕይወት ሲያጠፋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት አደረሰ

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሀረማያ ወረዳ እርሻ ማሳ ውስጥ የገባው ዝሆን የአንድ ሰው ሕይወት ሲያጠፋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታውቅቋል።የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮምንኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፍ ምክትል ኢንስፔክተር ካሲዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በዞኑ ሐረማያ ወረዳ በሊና ቀበሌ ውስጥ ድርጊቱ ተፈፅሟል።

የእርሻ ማሳ ውስጥ የገባው ዝሆን አቶ መሐመድ አሕመድ ቱሌ የተባሉትን የስምንት ልጆች አባት በኩንቢው ጠልፎ የጣላቸው ከእርሻ ማሳቸው ውስጥ ዝሆኑን  ለማውጣት ባደረጉት ጥረት እንደሆነ ገልፀዋል። በኩቢው አዛውንቱን ጠቅልሎ ከጣላቸው በኃላ በእግሩ ሲረጋግጣቸው የተመለከተው የሀያ አመት ወጣት አዛውንቱን ከዝሆኑ ጥቃት ለመታደግ ጥረት ሲያደርግ ዝሆኑ ጉዳት አድርሶበት እንደ ሄደ ገልፀዋል።

የአካባቢ ሰዎች ዝሆኑ ስፍራውን ለቆ ከሄደ በኋላ ሲደርሱ የአዛውንቱ ሕይወት ያለፈ ሲሆን ጉዳት የደረሰበትን ወጣት ደግሞ በሕይወት ያለ በመሆኑ ወዲያው ወደ ሀረማያ ሆስፒታል በማድረስ የሕክምና እርዳታ አግኝቶ በጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። 

ዝሆኖች አንዳንዴ ከባብሌ ፖርክ በመውጣት በሰብል ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሲሆን ይህንኑ ለመከላከል በሚደረግ ሙከራም በሰው ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ምክትል ኢኒስፔክተር  ካሲዪ አበበ ጨምረው ገልፀዋል።dagu

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.