Logo
Getu Temesgen
AFCON DAY -1
Viva Morocco ! viva The Atlas lions 🇲🇦
#ethiopia | አልካቢ ከራባት ሰማይ ስር በረረ ። የአትላስ አናብስቱም በድንቅ የመክፈቻ መሠናዶ ታጅበው በድል ጀመሩ ።

ካዛብላንካ ላይ እንደፈለጋችሁ ጠጡ ። ራባት ላይ በዳንኪራው ድመቁ ። ምክንያቱም ይህ የእናንተ ድንቅ የእግር ኳስ ምሽት ነው ። ይህ ከእግር ኳስ ኮሜንታተሩ ፒተር ዱሩሪ የተሰጠ የኳታር ዓለም ዋንጫ ሕያው የአድናቆት አይረሴ ቃል ለአትላስ አናብስቱም ዘንድሮ በአፍሪካ ዋንጫው ድግሳቸው የሚቀጥል መሠለ ። ሞሮኮ ዕዚህ አዱ ገነት ሸገር ኢትዮጵያ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ያሸነፈችው የአፍሪካ ዋንጫን ከ50 ዓመት በኋላ በእሯሳ ምድር የመጠበቅ ጫናውን ጭምር ተቋቁማ ለማሸነፍ አቅሙም ብቃቱም እንዳላት በመክፈቻው ፍንጭ ሰጠች ።

ሞሮኮ ዕጅግ ባመረ ደማቅ የአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ፕሮግራም የጀመረችው የኮሞሮስ ፍጥጫን ከራባት በአስተናጋጆቹ አሸናፊነት ተከፍቷል ። የሪያል ማድሪዱ ቤራሂሚ ዲያዝ እና ተቀይሮ የገባው አል ካቢ ድንቅ የመቀስ ምት ጎል የአፍሪካዊያኑ ታላቅ የእግር ኳስ ድግስ ተጀምሯል ። የሞሮኮው ልዑል አልጋወራሽን ጭምር ያስፈነደቀች ማራኪ ጎል ለውድድሩ ምርጥ ጎልነት ገና በመጀመሪያው ቀን የታጨች ሆናለች ። ሞሮኮም ምርጡን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ መክፈቻውን ከፍ አድርጋ በደማቅ መሠናዶ ሰቅላ ዓለምን አስገርማለች ። ሞሮኮ ያለ ዋና የፔዤው ኮኮቧ አችራፍ ሃኪሚ የአፍሪካ ዋንጫው የመክፈቻ ጨዋታ ግዳጇን በማራኪ የኤልካቢ የመቀስ ምት ጎል ባርካም ጀምራለች ። ከራባት ሰማይ ስር የበረረው የኦሎምፒያኮሱ ኮኮብ አልካቢ ጎል የአትላስ አናብስቱ ደጋፊዎችንም ያሰፈነደቀች ሆናለች ።

ነገ በDay -2 ማሊ ከዛምቢያ 11:00 የማዲባ ደቡብ አፍሪካ ከአንጎላ 2:00 ግብፅ ከዚምባቡዌ ምሽት 5:00 ይጫወታሉ ።

Tribune sport

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.