እስከ ዛሬ ያልተገለጠ የቱሪስት መዳረሻ፣ ናሲኦል ዋሻ
#ethiopia | ዋሻዎች ኃብትን፣ እውቀትንና ታሪክን በውስጣቸው የያዙ የሚስጢር ቋቶች ናቸው፡፡ ረጅሙ የሰው ልጆች የሕልውና ታሪክ የሚጀምረውም በዋሻዎች ውስጥ ነው፡፡
የዋሻ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ናስር አሕመድ÷ በምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ ባሌ እና አርሲ አካባቢዎች በርካታ አስደናቂ ዋሻዎች በብዛት እንደሚገኙ ይናገራሉ፡፡
ከ400 በላይ የሚሆኑትን ፈልጎ በማግኘትና በማጥናት በመጽሐፍ አሳትሞ ለዓለም ቱሪዝም ለማስተዋወቅ ሙከራ ያደረጉት ተመራማሪው÷ እነዚህን ዋሻዎች በተመለከቱበት ወቅት ለአንድ ልዩ ዋሻ የተለየ ፍቅር እንዳደረባቸው ያስረዳሉ፡፡
ይህ ዋሻ ናሲኦል በመባል የሚጠራ ሲሆን ÷ ዋሻውን ያገኙት፣ መርምረው ርዝመቱን የደረሱበትና በውስጡ ተጉዘው ውበቱን በመቅረጽ ለዋሻ አፍቃሪዎች ያስተዋወቁት ተመራማሪ አቶ ናስር ናቸው፡፡
የዋሻው ስያሜም ከተመራማሪው ስም በመነሳት የተሰጠ ነው፤ “ናሲኦል” የሚለው ስያሜ ትርጉሙ ከሁሉም የላቀ ማለት እንደሆነ አብራርተዋል።
በምስራቅ ሐረርጌ መልካ በሎ ወረዳ የተገኙት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቴሌቪዥን ዶክመንታሪ ቡድን አባላትም በዋሻው ውስጥ ከ500 ሜትር በላይ በመጓዝ የናሲኦልን ውበት በዓይናቸው ተመልክተው፤ በእጃቸው ዳስሰዋል፡፡
የዘርፉ ባለሙያዎች ዋሻዎች ካላቸው ባህርይ አንጻር የሕክምና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ፊዚዮቴራፒ እና የቱሪዝም ዋሻዎች በሚል እንደሚከፋፈሉ ያስረዳሉ።
በዚህ ረገድ በተለያዩ ሀገራት ተዘዋውረው ብዙ ዋሻዎችን የተመለከቱት አቶ ናስር በውበቱ ተወዳዳሪ እንደሌለው የመሰከሩለት ናሲኦል ከቱሪዝም ዋሻዎች ጎራ የሚመደብ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ይህንን ድንቅ ዋሻ እንደሚጎበኙት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
https://www.facebook.com/1...

6 months ago