በላይተር ሲጫወቱ የነበሩ ህፃናት መካከል እሳት በመነሳቱ የአንዲት ታዳጊ ህጻን ህይወት አለፈ
#ethiopia | ቤተሰቦቻቸው በሌሉበት ላይተር እሳት ማቀጣጠያ ይዘው ሲጫወቱ የነበሩ ሁለት ሕፃናት መካከል አንደኛዋ የለበሰችዉ ልብስ በለኮሱት የላይተር እሳት በመቀጣጠሉ ህይወቷ ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።
የምስራቅ ሐረርጌ ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙንኬሽ ፅህፈት ቤት ሐላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ እንደገለፁት በጃርሶ ወረዳ ወልተኢ ቀበሌ ወላጆቻቸው በሌሉበት የአምስት አመት ሴት ልጅ እና የስምንት ዓመት ወንድ ልጅ ላይተር እሳት ማቀጣጠያ እየለኮሱ ሲጫወቱ የነበሩ ሕፃናት መካከል የአምስት አመትዋ ሴት ልጅ ቀሚሷ በእሳት በመቀጣጠሉ የሚያጠፋላት ጠፍቶ በቃጠሎው ህይወቷ አልፏል።
አደጋው የደረሰው ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ሲሆን ላይተሩን የስምንት አመቱ ልጅ መለኮሱን የገለጹት ምክትል ኢንስፔክተር ካሳዬ በቃጠሎ የተጎዳችው ልጅ በጊዜው ወደ ጤና ተቋም ብታመራም መንገድ ላይ ህይወቷ ማለፉን ገልፀዋል።
ሁለቱ ሕፃናት ላይተሩን እየለኮሱ ሲጫወቱ ወላጆቻቸው በአጠገባቸው አለመኖራቸውንም ተነግሯል፤ወላጆች በእድሜ ያልበሰሉ ልጆች ፊት ተቀጣጣይ የሆኑ ነገሮችን ባያስቀምጡ እና ያለ ጠባቂ ብቻቸውን ጥለው መሄድ ለመሰል አደጋ እንደሚያጋልጥ ተመላክቷል።
ማንኛውም እድሜያቸው ከዘጠኝ አመት በታች የሆኑ ህፃናት በየትኛውም ወንጀል ተሳታፊ ቢሆኑም በህግ የሚጠየቁበት አግባብ እንደሌለ እና በወንጀሉ ድርጊት ለደረሰው ጉዳት የወንጀል አድራጊው ቤተሰብ ለተጎጂው ቤተሰብ ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤህግ ፅህፈት ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ሀላፊ አቃቤህግ አቢዮት አስፋው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

6 months ago