በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ ከሚደርሱ ጥቃቶች 35.2 በመቶ በትዳር አጋሮቻቸው ወይም አብረዋቸው በሚኖሩ ወንዶች የሚፈጸም መሆኑ ተነገረ
#ethiopia ||የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም “ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን አስቦ ውሏል።
በኢትዮጵያ በተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማያያዝ ፆታዊ ጥቃትን በጊዜና በቦታ ሳይወሰን ሁሉም ዜጋ መከላከል እንዳለበት የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አንለይ ወርቄ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፆታን መሰረት አድርጎ በሴቶች፣ ህፃናትና አካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈጸሙ በርካታ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ጾታዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች መኖራቸውን ተጠቁሟል፡፡
በኢትዮጵያ ከሚደርሱት ጥቃቶች ከ15 እስከ 49 በሆኑ ሴቶች ላይ 24.9 በመቶ አካላዊ፣ 24 በመቶ ስነልቦናዊ፣ 11.1 በመቶ ወሲባዊ፣ 28 በመቶ ወሲባዊ እና አካላዊ ጥቃት ይፈፀምባቸዋል መባሉን በተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አንለይ ወርቄ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም 35.2.በመቶ በትዳር አጋሮቻቸው ወይም አብረዋቸው በሚኖሩ ወንዶች ጥቃት ይፈጸምባቸዋል።#dagu

6 months ago