3 መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ በመተት በቤተሰብህ ላይ ጉዳት አደርሳለሁ እያለች ስታስፈራራ የነበረችን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች
ተጠርጣሪዋ አለምነሽ አጉማስ፤ ወንጀሉን ፈፅማለች የተባለው ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ወሎ ሰፈር አካባቢ ከሚገኝ አንድ ፕላዛ ውስጥ ነው።
ግለሰቧ በፕላዛው በጽዳት ሰራተኝነት እና በአሳንሰር ተቆጣጣሪነት ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን የግል ተበዳይ በዚሁ ህንጻ ላይ ከሚገኝ የአንድ የግል ድርጅት የፋይናስ ኃላፊ ናቸው።
የግል ተበዳይ አቶ ግሩም ነጋሽ ለፖሊስ በሰጡት ቃል እንዳስረዱት የኔሰው የሚባል ግለሰብ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ቢኮሎ ከሚባል አካባቢ እንደሚደውል ገልጸው 3መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ ልጅህን የሰይጣን መሳቢያ አደርጋታለሁ የሚል የማስፈራሪያ መልዕክት በማያውቁት ስልክ ተደውሎ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
የግል ተበዳዩ ያቀረቡትን አቤቱታ ተቀብሎ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና የተደወለበትን ስልክ እንዲሁም የማስፈራሪያ መልዕክት ያስተላለፈውን ሰው ድምፅ ማንነት ለመለየት በተደረገ ጥረት ተጠርጣሪዋ የግል ተበዳይን በመከታተል ካጠናች በኋላ ማንነቷን በመደበቅ እና ድምጿን በመቀየር አስፈራርታ 25ሺ ብር በባንክ እንዲያስገቡላት ካደረገች በኋላ ቀሪ 275ሺ ብር ለማስላክ ስትሞክር የግል ተበዳይ ለፖሊስ በሰጡት መረጃና ፖሊስ ባደረገው ጠንካራ ምርመራ ተጠርጣሪዋ ለመላክ ካዘጋጀችው የማስፈራሪያ ጽሑፍ የእጅ ስልኳ ላይ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት መሆኑን የላንቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።
አንዳንድ ግለሰቦች ሰዎችን በማጥናትና በባዕድ አምልኮ በማስፈራራት በቀላሉ ለመበልፀግ ጥረት እንደሚያደርጉ መገንዘብ እንደሚገባ ያሳሰበው ፖሊስ መሰል ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ነገሩን ከመደባበቅ ይልቅ በአስቸኳይ ወደ ፖሊስ በመሄድና መረጃ በመስጠት አጥፊዎች በህግ አግባብ እንዲጠየቁ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።dagu
seledadotio

6 months ago