በጭሮ "የፍቅር አጋር ሁኚኝ" ያላትን ሴት "እምቢ! "በማለቷ ለጥበቃ በተሰጠው መሳሪያ በመግደሉ የ57 አመቱ ሰው የ22 አመት እስራት ተፈረደበት
ወንጀለኛው የሟች አንድ ሴት ጓደኛንም በጥይት መቶ አቁስሏል።
የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምርያ መረጃ መሰረት ደብሩ ድሪባ የተባለው የ57 ዓመት ግለሠብ ነዋሪነቱ በጭሮ ከተማ ቡርቃ ጭሮ ቀበሌ ሲሆን በአንድ ድርጅት ውስጥ በጥበቃ ስራ ተቀጥሮ ይሰራል፡
ደብሩ ከዚሕ ቀደም ካለች ባለቤቱ ጋር ሶስት ልጆች አፍርቶ የተፋታ ሲሆን ከዛ በኋላ ብዙነሽ ሲሣይ ከተባለች የ35 ዓመት ሴት ጋር የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ሞክሮ ነበር።
ብዙነሽ ሲሳይም ቀደም ሲል ከነበራት ትዳር አንድ ልጅ የነበራት።
ብዙነሽ አዜብ ስዩሜና አዜብ ፍቅሬ ከተባሉ በእድሜ እኩያ ከሆኑ ወጣቶች ጋር ትውውቅ ጀምራ እየኖረች እያለ፤ደብሩ ደርቤ አብረን እንኑር የሚለው ጥያቄ ያቀርብላታል፡
ብዙነሽም የደብሩ ጥያቄን ከመቀበሏ በፊት ለሁለቱ ጓደኞቿ ሀሣቡን አቅርባ ከተነጋገሩበት በኃላ ጓደኞቿ ብቻሽን ከምትሆኚ አብራችሁ ብትኖሩ መልካም ነው በማለት ይመክሯታል።
ደብሩና ብዙነሽ በአንድ ጎጆ መኖር ይጀምራሉ፡፡
ይሁን እንጂ ብዙነሽ እንደ አሰበችው ከደብሩ ጋር ያላት ትዳር የተመቻቸ ባለመሆኑ ትታ ከቤቱ ትወጣለች።
በዚህ ግዜ ደብሩ ሁለቱን አዜቦች አስታርቁኝ ብሎ ሽምግልና ይልካል።የብዙነሽ ጓደኞች ለማስታረቅ ሙከራ ቢያደርጉም ብዙነሽ በገጠማት የጤና እክል ትታመማለች።
ደብሩ ግን "ታማ አይደልም አውቃ ነው"በሚል ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ላይ ለድርጅት ጥበቃ የተሠጠውን የጦር መሳርያ በመያዝ ታማ የተኛችውን ብዙነሽ ሲሳይ በአንድ ጥይት መቶ ሕይወትዋ እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡
በመቀጠልም በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት አዜብ ስዩሜ የተባለችውን የብዙነሽ ጓደኛ የምትሠራበት ቦታ ላይ ተኩሶ ጉዳት ያደርስባትና ከስፍራው ይሠወራል።
በዚሕም አላበቃም ሶስተኛ፣ አዜብ ፍቅሬ የተባለች ጓደኛዎን፣ለጥበቃ በተሠጠው መሣርያ ተኩሶ ለመምታት ሲል የጦር መሣርያው ይነክሣል።
በዚሕ ግዜ ጉዳት ሊደርስባት የነበረችው ሴት እየጮኽች የድረሱልኝ ጥሪ በማሰማት ስታመልጥ የፀጥታ አካላት ቀደሞ በተፈፀሙት ግድያ ና የግድያ ሙከራ ጉዳይ ክትትል ላይ በመሆናቸዉ ደብሩ ደርቤን በቁጥጥር ስር ያውሉታል።
ፖሊስ የሟች ብዙነሽ ሲሣይ አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል በመላክ አዜብ ስዩሜን በፍጥነት ለሕክምና በመላክ ህይወቷን ሊያተርፍ ችሏል።
ፖሊስ በተለያዩ ማስረጃዎች፣በአስክሬን ና በተጎጂዋ የሕክምና ማስረጃ እንዲሁም ወንጀል በተፈፀመበት የጦር መሣርያ ጭምር በማያያዝ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለአቃቢ ሕግ ላከ።
አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የሠው መግደል፣የአካል ማጉደል ና የመግደል ሙከራ ፣በድርብ ወንጀል ክስ ታሕሣስ 3 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ደብሩ ደርቤ በ 22 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

6 months ago