Logo
SeledaPost
እናት እና ልጅ ምሳ ከበሉ በኋላ ለጊዜው ባልታወቀ  ምክንያት  በተከታታይ ሰዓት ሕይወታቸው አለፈ

  👉 ፖሊስ  የአሟሟታቸውን ሑኔታ በጥልቅ እየመረመረ ይገኛል

እንደ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ገለፃ እናት እና ልጅ ምሳ ከበሉ በኋላ በተከታታይ ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል፡፡
 
እናት እና ልጅ ታህሣስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ አምስት ሰዓት ተኩል መስጊድ ሰላት ቆይተው ወደቤታቸው ገብተው ምሳቸውን ከበሉ በኋላ እናት ሻወር ለመውሰድ ሻወር ቤት ሲደርሱ አረፋ በመድፈቅ እና በመወራጨት ሲወድቁ የተመለከተች ልጅ በድንጋጤ በመጮህ የአካባቢው ሠው ሲደርስ ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጥዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰዓት ቆይታ በኃላም ልጅ እንደ እናቷ ከአፏ አረፋ በመድፈቅ ስትወድቅ ወደ ካራሚሌ ሆስፒታል ለህክምና ብትላክም በህክምና ላይ እያለች ህይወቷ አልፏል።ፖሊስ የሟቾችን አስክሬን ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የላከ ሲሆን በተጨማሪ ለምሳ የተመገቡትን ምግብ እና የጠጡትን ውሀ ናሙና ለኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለ ስልጣን በመላክ ስለ አሟሟታቸው ምክንያት ሰፊና ጥልቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.