Logo
FIDEL POST NEWS
በምስራቅ ሀረርጌ ከመስጂድ መልስ እናት እና ልጅ ምሳ ከበሉ በኋላ በሰአታት ልዩነት አረፋ ደፍቀው ህይወታቸው አለፈ

👉ለምሳ የተመገቡት ምግብ እንዲሁም የጠጡት ውሀ ናሙና ለኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለ ስልጣን ተልኳል።

ታህሣስ 3, 2018 ዓ.ም እናት እና ልጅ እኩለ ቀን አካባቢ መስጂድ ሰላት አድርገው ወደቤታቸው ገብተው ምሳቸውን በሉ ።

እናት ገላዋን ለመታጠብ መታጠቢያ ቤት ስትደርስ አረፋ በመድፈቅ እና በመወራጨት ወደቀች።

ልጅ በድንጋጤ በመጮህ ለእርዳታ ጎረቤት ጠራች።የአካባቢው ሠው ተደናግጦ በቦታው ሲደርስ እናት ህይወቷ አልፎ ነበር ሲሉ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ገልፀዋል።

ከእናቷ ህልፈት ከሰዓት ቆይታ በኃላም ልጅ እንደ እናቷ ከአፏ አረፋ በመድፈቅ ወደቀች ። ወደ ካራሚሌ ሆስፒታል ለህክምና ብትላክም በህክምና ላይ እያለች ህይወቷ ማለፉን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል።

ፖሊስ የሟቾችን አስክሬን ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የላከ ሲሆን በተጨማሪ ለምሳ የተመገቡትን ምግብ እና የጠጡትን ውሀ ናሙና ለኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለ ስልጣን በመላክ ስለ አሟሟታቸው ምክንያት ምርመራ እያደረገ ነው ተብሏል።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.