ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ያለውን ስራ ለማስፋፋት 138 ሚሊየን ዶላር ተበድሯል
#ethiopia | የቴሌኮም ገበያው ለውጪ ተቋማት ክፍት መሆኑን ተከትሎ ከጥቂት አመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ የገባው ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ያለውን ስራ ለማስፋፋት ከስታንዳርድ ባንክ 138 ሚሊየን ዶላር ተበድሯል።
ሳፋሪኮም ባገኘው ብድር በኢትዮጵያ የዲጂታል አገልግሎቶችን እና መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት እንደሚሰራ ተነግሯል።
ስታንዳርድ ባንክ ሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲቀላቀል አማካሪና የገንዘብ ፈንድ ያደረገ ባንክ ሲሆን በሃብት(Assets )የአፍሪካ ግዙፉ ባንክ ነው።
የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንዴግዋ አላማቸው ወጣቶች፣ ስራ ፈጣሪዎች እና የተገለሉ ማህበረሰቦች በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንዲሳተፉ በማድረግና በ2030 የታሰበው የጋራ ብልፅግና እንዲደረስ የብዙሃንን ህይወት መለወጥ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊየን በላይ ንቁ ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን የ4ጂ የኢንተርኔት አገልግሎቱን ለግማሽ ያህሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተደራሽ አድርጓል።
ወደ ኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ከገባ በኋላ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮም እና የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት መሰረተ ልማቶች ላይም ከ2.27 ቢሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት አድርጓል።#tm

6 months ago