አውስትራሊያ በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ ክልከላ ልትጀምር ነው
አውስትራሊያ የህጻናትን የኦንላይን ደህንነት ለመጠበቅ በማሰብ በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን እና ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ መጠቀምን የሚከለክለውን ህግ ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር ታወቀ።
ይህ አዲስ ህግ እንደ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲክቶክ፣ ስናፕቻት፣ ዩቲዩብ እና ኤክስ (ትዊተር) ያሉ ታላላቅ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በቀጥታ የሚመለከት ነው።
በእነዚህ መተግበሪያዎች ላይ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት አዲስ አካውንት እንዳይከፍቱ እና ነባር አካውንቶችም እንዲዘጉ የማድረግ ግዴታ በኩባንያዎቹ ላይ ተጥሏል።
የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎቹ ይህንን ህግ ተላልፈው ከተገኙ ወይም በቂ የመቆጣጠሪያ እርምጃ ካልወሰዱ እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
ማንኛውም ተጠቃሚ ዕድሜውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል የተባለ ሲሆን፤ ህጉ ግን እንደ ዋትስአፕ፣ ዩቲዩብ ኪድስ፣ ጉግል ክላስሩም እና ሮብሎክስ ያሉ ለትምህርት እና ለመልእክት ልውውጥ የሚያገለግሉ መተግበሪያዎችን እንደማይመለከት ተገልጿል።
ምንም እንኳን ህጉ የህግ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም፤ የአውስትራሊያ መንግስት ግን ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ከመሆን እንደማይታገድ አስታውቋል።
Ethio Fm

6 months ago