ጃፓን ተርገፈገፈች ! ከባዱ አደጋ እየመጣ ነዉ ተባለ !
ባለፉት አስር ዓመታት ዉስጥ ብቻ ተፈጥሯዊ አደጋዎች ደጋግሞ የጎበኛት በምድሪቱ መሬት መንቀጥቀጥና ሱናሚ ግንባር ቀደም ተጋላጭ የሆነችው ጃፓን በሬክተር መለኪያ 7.5 የደረሰ መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተዘግቧል።
ባለስልጣናቱ ማክሰኞ ዕለት እንደገለፁት ከሆነ ሰኞ እለት ከምሽቱ 11፡15 (14፡15 GMT) በሰሜን ምስራቅ ጃፓን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 30 ሰዎችን ቆስሏል፣ መንገዶችን አበላሽቷል የገበያ ማዕከላትን አዉድሟል በዚህ የበረዶ ወቅት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ በመዉደሙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች በብርድና ቅዝቃዜ ተዳርጓል ብለዋል።
የጃፓን ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ (JMA)
የመንቀጥቀጡ ማዕከል ከአኦሞሪ ግዛት የባህር ዳርቻ 80 ኪ.ሜ (50 ማይል) ርቀት ላይ በ50 ኪ.ሜ (30 ማይል) ጥልቀት ላይ እንደነበር ከ20 እስከ 70 ሴ.ሜ (7 እስከ 27 ኢንች) ከፍታ ያላቸው ሱናሚዎች ታይተዋል ሲል ዘግቧል።
(JMA) አክሎም የመሬት መንቀጥቀጡ በዚህ አያበቃም በቀጣይ ቀናት ከባህር በኋላ እስከ 3 ሜትር (10 ጫማ) የሚደርስ ሱናሚ የጃፓንን ሰሜን ምስራቅ የባህር ዳርቻ ሊመታ እንደሚችል ተናግሯል።
በሆካይዶ፣ አኦሞሪ እና ኢዋቴ ግዛቶች ላይ የሱናሚ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥተዋል ።
የእሳት አደጋ እና የአደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ 23 ሰዎች ቆስለዋል ሲል የሕዝብ ብሮድካስት ኤን ኤችኬ ዘግቧል።
አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች በወደቁ ነገሮች ተመትተዋል፣ በርካታ ሰዎች በሃቺኖሄ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ቆስለዋል ብሏል ።
የፓስፊክ ሱናሚ ማስጠንቀቂያ ማዕከል “ከሆካይዶ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚመጡ አደገኛ የሱናሚ ሞገዶች በጃፓን እና በሩሲያ የባህር ዳርቻዎች 1,000 ኪ.ሜ (620 ማይል) ርቀት ላይ ሊኖሩ ይችላሉ” ብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ታኪቺ በተጎዱ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በፍጥነት እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል።
የካቢኔ ዋና ፀሐፊ ሚኑሩ ኪሃራ ወደ 800 የሚጠጉ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል የሌላቸው ሲሆኑ፣ ወደ 480 የሚጠጉ ነዋሪዎች ደግሞ በሃቺኖሄ አየር ማረፊያ መጠለያ እየወሰዱ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያ እስኪነሳ ድረስ መጠለያ ወይም ከፍ ያለ ቦታ እንዲፈልጉ አሳስበዋል።
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በበኩሉ (IAEA) በፉኩሺማ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ምንም አይነት ያልተለመደ ነገር እንዳላየ ተናግሯል።
በየዓመቱ ወደ 1,500 የሚጠጉ የመሬት መንቀጥቀጦች የምታስተናግደው ጃፓን በፓስፊክ "የእሳት ቀለበት" ምዕራባዊ ጫፍ ላይ በሚገኙ አራት ዋና ዋና የቴክቶኒክ ሳህኖች አናት ላይ የምትገኝ ሲሆን ለተፈጥሮ አደጋ በዓለም ላይ በጣም ተጋላጭ ናት ።
የጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ ታሪክ
እ.ኤ.አ. በ2011፣ በ9.0 የሚደርስ የመሬት መንቀጥቀጥ 18,500 ሰዎችን ለሞት ወይም ለአካል ጉዳት እና በፉኩሺማ የኑክሌር ማመንጫ ላይ ከባድ የቃጠሎ አደጋ አስከትሏል። ለዘገባዉ አልጀዚራን ኢንዲያን ታይምስን ተጠቅመናል ።

6 months ago