Logo
Getu Temesgen
በፓኪስታን እና በአፍጋኒስታን መካከል የድንበር ጦርነት ተቀሰቀሰ
#ethiopia | በፓኪስታን እና በአፍጋኒስታን ታሊባን ሃይሎች መካከል የድንበር ግጭት እንደገና ተቀስቅሷል ፣እያንዳንዱ ወገን ሌላኛውን አካል ደካማ የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነቱን አፍርሷል በሚል እየተካሰሱ ይገኛሉ።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው 2,600 ኪሜ ድንበር ላይ የምትገኘውን የአፍጋኒስታን ከተማ ስፒን ቦልዳክን ነዋሪዎች ጥቃትን ፈርተው ተሰደዋል።

በአቅራቢያው በምትገኘው የካንዳሃር ከተማ የህክምና ሰራተኛ ለቢቢሲ ፓሽቶ አገልግሎት እንደተናገሩት አራት አስከሬኖች በአካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል ገብተዋል። ሌሎች አራት ሰዎች ቆስለዋል። በፓኪስታን በኩል ደግሞ 3 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል።

ባለፉት ወራት በሁለቱ ሀገራት መካከል አልፎ አልፎ ጦርነት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፥ የአፍጋኒስታኑ የታሊባን መንግስት ፓኪስታን በሀገሪቱ ውስጥ የአየር ድብደባ ትፈጽማለች ሲል ከሷል።

ሁለቱም ወገኖች የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ቢያረጋግጡም ለአራት ሰአታት የፈጀውን ጦርነት በተመለከተ አንዳው ሌላኛውን ለጥቃቱ ወቅሰዋል።

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትር ሸህባዝ ሻሪፍ ቃል አቀባይ ሞሻራፍ ዛዲ ታሊባንን “ያለምክንያት ተኩስ ከፍቷል” ሲሉ ከሰዋል። ይህንኑ ተከትሎ “አፋጣኝ፣ ተገቢ እና ጠንከር ያለ ምላሽ በታጣቂ ሃይሎቻችን ተሰጥቷል ብለዋል። ፓኪስታን ግዛቷን እና የዜጎቻችንን ደህንነት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነች ሲሉ አክለዋል።#dagu

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.