Logo
FIDEL POST NEWS
የሩሲያ ሳይንቲስት በሀገር ክህደት ወንጀል የ21 ዓመት እስራት ተፈረደበት

​አንድ ሳይንቲስት የሩሲያ ብሔራዊ ደኅንነት ህጎችን በመጣስ ከፍተኛ የእስር ቅጣት ተላልፎበታል። የሞስኮ ፍርድ ቤት የፊዚክስ ሊቅ የሆነውን አርቴም ኮሮሺሎቭን በክህደት ወንጀል የ21 ዓመት እስራት እንደቀጣው የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

​የ34 ዓመቱ ኮሮሺሎቭ በታኅሣሥ ወር 2023 በሶስት ክሶች ተከሶ ነበር። ከተከሰሱባቸው ጉዳዮች መካከል፡-

​በዩክሬን ስም በሩሲያ ወሳኝ መሠረተ ልማት ላይ የDDoS ሳይበር ጥቃት ማድረስ፣
​ለዩክሬን ጦር ገንዘብ መላክ፣ እና
​ስለ ሩሲያ ጦር ሚስጥራዊ መረጃ መሰብሰብ ይገኙበታል።

​እንደ ሚዲያዞና ዘገባ፣ ኮሮሺሎቭ አንዳንድ ክሶችን አምነው የተቀበሉ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2022 በሩሲያ ፖስት ሰርቨር ላይ በደረሰው የDDoS ጥቃት ላይ ግን በቀጥታ ተሳትፎ እንደሌላቸው አስተባብለዋል።

​ባለፈው ሳምንት ለፍርድ ቤቱ በሰጠው የመጨረሻ ቃል፣ ኮሮሺሎቭ የሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችው ወረራ “የግል መጥፎ አጋጣሚ” እንደሆነ ገልፆ ብዙ የቤተሰቡ አባላት በዩክሬን እንደሚኖሩ ተናግሯል

​ሐሙስ ዕለት ፍርድ ቤቱ በሀገር ክህደት፣ በወሳኝ መሠረተ ልማት ላይ ጥቃት በማድረስ፣ ፈንጂዎችን በመያዝ እና የማበላሸት ድርጊት በማቀድ ወንጀለኛ አድርጎ አግኝቷቸዋል። ዓቃቤ ህግ የ25 ዓመት እስራት እንዲወሰንባቸው ጠይቆ ነበር።
​በሩሲያ ውስጥ ከብሔራዊ ደኅንነት ጋር የተያያዙ የክህደትና የስለላ ክሶች በዝግ ይካሄዳሉ።

​ኮሮሺሎቭ ከሞስኮ የፊዚክስና ቴክኖሎጂ ተቋም (MIPT) የተመረቀ ሲሆን፣ በሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የጠቅላላ ፊዚክስ ተቋም ተመራማሪ ሆኖ ይሰራ ነበር።
​
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.