የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ዓብይ ጉባኤ ለ117 ዳኞች ሹመት ለክልሉ ምክር ቤት ኡቀረበ
👉 የሁለት ዳኞች ያለመከሰስ ከለላ ተነስቷል
#ethiopia | የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ዐቢይ ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔ መስጠቱ ተገልጿል። በዚህም 169 የወረዳ ፍርድ ቤት ረዳት ዳኞች እና 5 የአዲስ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች በድምሩ የ174 ዳኞች ሹመት ለክልሉ ምክር ቤት እንዲቀርብ መወሰኑ ተገልጿል፡፡
አራት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሸሪዓ ዳኞች እና 25 የወረዳ ፍርድ ቤት ሸሪዓ ዳኞች ሹመት ሰጥቷል። እንዲሁም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ እና ጎንደር ምድብ ችሎት አስተባባሪዎች ከኃላፊነት እንዲነሱ ወስኗል።
የአንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የተጠረጠሩበትን ሃሰተኛ ሰነድ እና የአንድ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ የተጠረጠሩበትን የአካል ጉዳት ማድረስ እና ዛቻ ወንጀል መነሻ በማድረግ ከተወያየ በኋላ ያለመከሰስ ከለላቸዉን ማንሳቱ ተገልጿል።
እንዲሁም የፀባይ እና የስነስርዐት ጉዳዮችን መርምሮ ሁለት የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ከኃላፊነት እንዲነሱና ውሳኔው በክልሉ ምክር ቤት እንዲጸድቅ የውሳኔ ሀሳብ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በሌሎች የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ መክሮ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ሌሎች የቅሬታ ይግባኞችን መርምሮ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልጋቸው የዲሲፒሊን ጉዳዮች በቀጣይ ጉባኤ ተጣርተው እንዲቀርቡ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
በተጨማሪም የቀረበለትን የዝውውር መረጃ መርምሮ ለኅብረተሰቡ የተሻለ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ሲባል በጥናት ላይ የተመሰረተ የመመሪያ ማሻሻያ ተደርጎ እስኪተገበር ድረስ መደበኛ ዝውውር ለጊዜዉ ታግዶ እንዲቆይ እና በሚወጣው መመሪያ መሰረት ውድድር ተደርጎ እንዲተገበር ሆኖም እንደአስፈላጊነቱ በልዩ ዝውውር የሚቀርቡ የዝውውር ጥያቄዎች እንዲስተናገዱ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡#dagu

7 months ago