Logo
Getu Temesgen
የኬንያ መንግስት በሳፋሪኮም ውስጥ ያለውን ድርሻ ሊሸጥ ነው
#ethiopia | ኬንያ በሳፋሪኮም ውስጥ ያላትን የ15% ድርሻ ለደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም በ1.6 ቢሊየን ዶላር ልትሸጥ ነው።

ውሳኔው በኬንያ የፋይናንስ ሚኒስትር ይፋ ሲሆን የመንግስት ድርጅቶችን በመሸጥ ገንዘብ ማግኘትም ምክንያት ነው ተብሏል።

የኬንያ መንግስት 40 በመቶ ገቢውን እዳ ለመክፈል እያዋለው ሲሆን ይህ ሽያጭም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ነው።

ቮዳኮም የሳፋሪኮምን የ39.9% ባለድርሻ ሲሆን የኬንያ የፋይናንስ ሚኒስትር ከሳፋሪኮም ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ያለ ተጨማሪ ብድር በመንገድ፣ በኃይል እንደዚሁም በኤርፖርት ስራ ኢንቨስት ለማድረግ ወደተቋቋሙት የብሔራዊ መሰረተ ልማት ፈንድና የሃብት ፈንድ( Sovereign Wealth Fund) ይገባል ብሏል።

የሳፋሪኮም ሽያጭ የፓርላማ ውሳኔ ብቻ ቀርቶታል ሲባል በተጨማሪም በቀጣይ አመት በኬንያ ነዳጅ የማሰራጨት ስራ የሚሰራው መንግስታዊ ተቋም ድርሻ ለህዝብ መሸጥ ይጀምራል።

ግዢው በፓርላማ ከፀደቀ ቮዳኮም የሳፋሪኮምን 55 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ የኬንያ መንግስት ድርሻ ወደ 20 በመቶ ይቀንሳል። ቀሪው 25 በመቶ ድርሻ ደግሞ በተለያዩ ኢንቨስተሮች የተያዘ ይሆናል።#ሮይተርስ

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.