ጋዜጠኛ ደምስ መኩሪያው በምርጥ የሳይንስ ዘገባዎች ዘርፍ ተሸለመ
#ethiopia | በኢቢሲ በውጭ ቋንቋዎች ዜና እና ወቅታዊ ዲፓርትመንት በዋና አዘጋጅነት የሚሰራው ጋዜጠኛ ደምስ መኩሪያው፣ በምርጥ የሳይንስ ዘገባዎች ዘርፍ የክብር ተሸላሚ ሆኗል።
ጋዜጠኛ ደምስ በሰራው ዘገባ የገንዘብና የክብር ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀውና በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ እየተካሄደ ባለው 13ኛው የዓለም ሳይንስ ጋዜጠኞች ጉባኤ፣ በአፍሪካ በሳይንስ ዘርፍ የተሻሉ ዘገባዎችን የሰሩ ጋዜጠኞች መሸለማቸው ተጠቁሟል።
ጋዜጠኛው ለውድድር ያቀረበው ዘገባ የጣና ሃይቅን ከእንቦጭ ወረራ ለመታደግ በኢትዮጵያ እየተወሰዱ ያሉ ሳይንሳዊና ስነ-ሕይወታዊ መፍትሄዎችን የሚዳስስ ነው ተብሏል።
ጋዜጠኛው ከዚህ ቀደምም እ.ኤ.አ በ2018 በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደ ውድድር የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ የአየር ንብረት ዘጋቢ በሚል ሽልማት ማግኘቱን ኢቢሲ በዘገበው አስታውሷል።

10 months ago