ለኩላሊት እጥበት ህክምና አገልግሎት የጤና መድህን ሽፋን አይሰጥም ተባለ
👉 በኢትዮጵያ 84 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና ተጠቃሚ ሆኗል
በተለያዩ አጋጣሚዎች ለውጪ ሀገር ህክምና ፤በስራ ተቋማት ውስጥ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፤ሶስተኛ ወገን ሽፋን ያላቸው ፤ ለኩላሊት እጥበት ታካሚዎች እና ለውበት መጠበቂያ ለሚወጡ ህክምናዎች በጤና መድህን ሽፋን ማግኘት እንደማይቻል የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት አስታውቋል ፡፡
የጤና እክል አጋጥሞት ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ እንዲታከም ለሚደረግ ታካሚ በጤና መድህን የተሰበሰበውን ገንዘብ አንድ ሰው ላይ ማዋል እንደሆነ እና ፍትሀዊ አገልግሎት አሰጣጥ እንደማይሆን ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳምጠው ጥላሁን ናቸው፡፡እንዲሁም ለኩላሊት ህመምተኞች ለሚደረግ የእጥበት አገልግሎት ላይም የጤና አገልግሎት የጤና መድህን ሽፋን መስጠት አስቸ ጋሪ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ከእነዚህ ህክምናዎች ውጪ ግን ምንም አይነት የገንዘብ ገደብ ሳይደረግ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ 84 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የማህበረሰብ አቀፍ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት በ1ሺ195 ወረዳዎች ስር ከ4ሺ347 ጤና ተቋማት ጋር ውል በማሰር የጤና ተቋማቱ ለማህበራዊ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች የዱቤ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡ በመጨረሻም ኦዲት ተደርጎ ለጤና ተቋማቱ ክፍያው እንደሚፈፀምላቸው ገልፀዋል ፡፡በ2018 ዓ.ም ደግሞ የወረዳ ሽፋኑን አሳድጎ ለ1ሺ320 ወረዳ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ማቀዱን በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳምጠው ጥላሁን ጨምረው ተናግረዋል፡፡
Dagu
seledadotio

7 months ago