Logo
FIDEL POST NEWS
ዊትኮፍ ክሬምሊን ገቡ። ሰአት ወደ ታች መቁጠሩ ተጀምረ

​እሳቸውና ጃሬድ ኩሽነር ከፑቲን ጋር በድርድር ላይ ናቸው።

​የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን ለማቆም ድርድሩን ለማፋጠን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ንግግሮች ለማድረግ ክሬምሊን ገብተዋል።

​ከእሳቸው ጋር አብረው ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አማች የሆኑት እና በጋዛ ሰላምን በማምጣት ረገድም ቁልፍ ሚና የተጫወቱት ጃሬድ ኩሽነር መሆናቸውን የሩሲያ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

​ሁለቱ አሜሪካውያን በአውሮፕላን ማረፊያ የተቀበሏቸው የሩሲያ የኢንቨስትመንት ፈንድ ኃላፊ ኪሪል ዲሚትሪየቭ ናቸው፣ ነገር ግን ከሩሲያ በኩል በስብሰባው ላይ የሚገኙት ፑቲን እና አስተርጓሚ ብቻ ናቸው።

​የTASS ዘገባ መሰረት የሩሲያ መንግስት ቃል አቀባይ ፔስኮቭ በሰጡት መግለጫ ላይ ሦስቱ ብቻ ንግግር እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

​ዊትኮፍ በጄኔቫ እና ፍሎሪዳ በተደረጉት የቅርብ ጊዜ ድርድሮች ዙሪያ የተዘጋጀውን የአሜሪካ-ዩክሬን የሥራ ማዕቀፍ የቅርብ ጊዜ እትም ለፑቲን ያቀርባሉ።
​ፔስኮቭ በተጨማሪም ሞስኮ ለሰላም ንግግሮች ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል፣ ነገር ግን ግቦቿን ማሳካት እንዳለባት አሳስበዋል።
​ዲሚትሪየቭ ዛሬን ለዓለም አስፈላጊ ቀን ነው ሲሉ ጠርተውታል።

​“ለዓለም አስፈላጊ ቀን ነው፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን የጋዛ የሰላም ስምምነት ያዘጋጀው ቡድን የትራምፕን የሰላም አጀንዳ በዩክሬን ለማስቀጠል ወደ ሞስኮ ይመጣሉ” ብለዋል።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.