በምዕራብ ሀረርጌ ዶልፊን ከቦቴ መኪና ጋር ተጋጭቶ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ
በዶልፊኑ ውስጥ የነበሩት ሁሉም ሰዎች ሞተዋል። የቦቴው ሹፌር ተሰውሯል። ፖሊስ እየፈለገው ነው።
ዶልፊኑ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚመጣ የነዳጅ ማመላሻ መኪና ጋር ተጋጨ። ዶልፍኗ ውስጥ የነበሩት የስምንት ወንዶችና የሶስት ሴቶች ህይወት አልፏል።
የዶልፊኑ ሾፌር እና ረዳትም ስም ከማቾቹ መዝገቡ ውስጥ ነው።
አደጋው የደረሰው ትናንት ህዳር 20,2018 ዓ. ም. ከቀኑ አስር ሰአት ላይ ሲሆን መነሻውን ከሚኤሶን ከተማ ያደረገ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-96835 ኦሮ ዳልፊን የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ዘጠኝ ተሣፋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አዋሽ ከተማ ሲጓዝ በተቃራኒ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-ኤ-11805 ኢቲ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ቁቢ ቦርደዴ ወረዳ ጨቱ ቀበሌ በተባለ ስፍራ ፊት ለፊት በመጋጨቱ ነው።
የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ አንደገለፀው የአደጋው መንስኤ የዶልፊኑ ተሽከርካሪው መስመሩን ለቆ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ና ፊት ለፊት ከነዳጅ ጫኝ ቦቴው ጋር በመጋጨቱ ሲሆን የነዳጅ ቦቴ አሽከርካሪው ለግዜው ተሰውሯል።
ፖሊስ ከተሽከርካሪው ውስጥ የመንጃ ፈቃዱንና ሌሎች መረጃዎችን በማግኘቱ ክትትል ላይ መሆኑ ተገልፇል።
የሟቾች አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ፖሊስ ገልፇል።

7 months ago