Logo
Getu Temesgen
በዛሬው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ በአንድ ዶልፊን ውስጥ የነበሩ 11 ሰዎች ሰዎች ህይወት አለፈ

📌 ከአደጋው የተረፈ ተሳፋሪ የለም
#ethiopia | በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉቢ ቦርደዴ ወረዳ በዛሬው እለት አስር ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ ዶልፊን ያሳፈራቸው አስራ አንድ ሠዎች ህይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ አስታውቋል።

የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የትራፊክ ደሕንነት ና ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ዳኙ ሶሪ ለብስራት ሬዲዬ እንደተናገሩት ዛሬ ህዳር 20 ቀን 2018 ዓም መነሻውን ከሚኤሶን ከተማ ያደረገ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-96835 ኦሮ ዳልፊን የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ዘጠኝ ተሣፋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አዋሽ ከተማ ሲጓዝ ነበር።

ተሸከርካሪው በተቃራኒ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-ኤ-11805 ኢቲ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ቁቢ ቦርደዴ ወረዳ ጨቱ ቀበሌ በተባለ ስፍራ ፊት ለፊት ተጋጭተዋል።

በአደጋው በዶልፊኑ ውስጥ የነበሩ አሽከርካሪውን እና ረዳቱን ጨምሮ የስምንት ወንዶችና የሶስት ሴቶች በአጠቃላይ ተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።

የአደጋው መንሴ የዶልፊኑ ተሽከርካሪው መስመሩን ለቆ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ና ፊት ለፊት ከነዳጅ ጫኝ ቦቴው ጋር በመጋጨቱ ሲሆን የነዳጅ ቦቴ አሽከርካሪው ለግዜው ተሰውሯል።

ፖሊስ ከተሽከርካሪው ውስጥ የመንጃ ፈቃዱን ና ሌሎች መረጃዎችን በማግኘቱ ክትትል ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

የሟቾች አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል የተላከ ሲሆን በአንድ አደጋ ሙሉ ተሳፋሪ ህይወቱ ያለፈበት አጋጣሚ ከዚህ ቀደም የተመዘገበ እንደሌለ ምክትል ኢንስፔክተር ዳኙ ሶሪ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.