Logo
SeledaPost
"የራስን የባሕር በር ማግኘት የሚባለው አጀንዳ አደገኛ ነው" - ኤርትራ-

የኢትዮጵያው ገዥ ብልጽግና ፓርቲ፣ ቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ የባሕር ኃይል ጣቢያ የማቋቋም ፍላጎቱ "የደኅንነት አመክንዮም" ሆነ "የደኅንነት ትሩፋት" የለውም ሲሉ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አጣጣሉ።

የጉዳዩ ዋና ውዝግብ የባሕር በር አይደለም ያሉት የማነ፣ ኢትዮጵያ ለንግድ አገልግሎት አዋጭ የሆኑ ስምምነቶች ላይ ለመድረስ በርካታ አማራጮች አሏት ብለዋል።

የማነ፣ "የራስን የባሕር በር ማግኘት" የሚባለው አጀንዳ ግን "አደገኛ" እና "የኢትዮጵያ ጎረቤቶችን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የሚጥስ" መሆኑን ገልጸዋል።

"ሌላኛው የብልጽግና ፓርቲ አስገራሚ የራስን የባሕር በር ጥያቄ፣ ቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ የባሕር ኃይል ጣቢያ ለማቋቋም ፍላጎት ያለው መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጡ ነው" ሲሉም ተችተዋል።

የንግድ ልውውጡን በቀይ ባሕር በኩል የሚያደርግ ማንኛውም አገር ቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ የባሕር ኃይል ጣቢያ የማቋቋም ሕጋዊ መብት ይኖረዋል ማለት እንዳልሆነም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የውጭ ወታደራዊ አዛዦች በአዲስ አበባ አንዳንድ ጊዜ የሚያደርጓቸውን "ተራ" ጉብኝቶች አጣሞ የማቅረብ አሰልቺ አካሄድ ጀምሯል በማለት የማነ አያይዘው የተቹ ሲሆን፣ ፓርቲው የአሜሪካው የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ እንዲሁም የጣሊያን ባሕር ኃይልና የፈረንሳይ ጦር ኃይል አዛዦች በኢትዮጵያ ያደረጓቸው ጉብኝቶች የባሕር በር የማግኘት ፍላጎቱን የሚደግፉ አስመስሎ አቅርቧቸዋል ማለታቸውን ዋዜማ ሬዲዮ ዘግባለች፡፡

seledadotio
seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.