በወተት ላይ መርዝ በመጨመር የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ግለሰቦችን የገደሉ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
ተከሳሾቹ ሳራ መሃመድ ፣ሂንድያ አረባ ፣አብድራማን አብዲ የተባሉ ሶስት ግለሰቦች ነዋሪነታቸው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ ሐቃ ቀበሌ ነው። ግለሰቦቹ አብድር አማን ከሚባል ጎረቤታቸው ጋር ከዚህ ቀደም ሰላማዊ የሆነ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የሚያጋጨው ነገር ተፈጠረ።ዋነኛ የቅራኔ ምክንያታቸዉ በጫት እርሻ ላይ የተፈጠረ የመሬት ግጭት ሲሆን ይህም ተካሮ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓም ላይ ወደ ኃይለኛ ፀብ አምርቶ በአካባቢ ሰዎች ግልግል የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ነገሮች ይረግባሉ።
ነገር ግን ሶስት ጎረቤቶች ማታ ላይ ተሰባስበው በተፈጠረው ፀብ ምክንያት ተወያይተውና ተመካክረው አንድ ነገር ለማድረግ ውሳኔ ላይ ደረሱ።በነጋታውም መጋቢት 17ቀን 2017 ዓም ጠዋት አራት ሰዓት ላይ የአቶ አብድር አማን ቤተሠቦች በሌሉበት ሶስቱ ተከሳሾች የተዘጋ በር ከፍተው በመግባት ለጫት እርሻ የተዘጋጀ ፀረ አረም መድኃኒት በመያዝ በወተት ማጠራቀምያ ያለ ወተት ውስጥ በመጨመር እንደነበረ ከዳድነው የቤቱን በር ዘግተው ይወጣሉ።ከቀኑ አስር ሠዓት ላይ የአቶ አብደር አማን ቤተሠብ መካከል የአርባ አምስት ሴት፣የአስራ ሁለት አመት ታዳጊና የሁለት አመት ልጅ በፀረ አረም መድሐኒት የተበከለው ወተት ከማጠራቀሚያ ውስጥ አውጥተው እየቀዱ ሶስቱም መጠጣት እንደጀመሩ የጉርሱም ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ስንታየኁ አይደፈር ተናግረዋል።
በፀረ አረም መድሐኒት የተመረዘውን ወተት ከጠጡት መካከል የሑለት አመቱ ልጅ ከሠአታት በሗላ በሆድ ቁርጠት ና ማስመለስ ሲታመም ወደ ጤና ጣቢያ ሣይደርስ ሕይወቱ ማለፉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡ከሰዓታት ቆይታም በኋላም የ12 ዓመቷ ታዳጊ በተመሳሳይ መንገድ በሆድ ቁርጠት ና ማስመለስ ህመም በሕክምና ላይ እያለች ህይወቷ ያልፋል።በነጋታው ደግሞ ሶስተኛዋ የአርባ አምስት ዓመት ሴት የሕክምና እርዳታ ላይ እያለች ህይወቷ ያልፋል።ፖሊስ፣ የሶሰት ሰዎች ሕይወት የጠፋበትን ምክንያት ለማረጋገጥ የአስክሬን ምርመራ ከማድረግ ባሻገር በፀረ አረም መድኃኒት የተበከለውን ወተት ለኢትዮጵያ የምግብ ና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በመላክ ባገኘው የምርመራ ውጤት ለምርመራ የተላከው የወተት ናሙና እጅግ አደገኛ በሆነ መርዛማ የአረምc መድኃኒት የተበከለ መሆኑን ማረጋገጫ እንደደረሰው ኢንስፔክተር ስንታየሁ ገልፀዋል።
ድርጊቱን ማን ሊፈፅም ይችላል ተብሎ በፖሊስ በኩል የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ በተደረገው ማጣራት ሶስቱ ጎረቤታሞች በቁጥጥር ሲውሉ ፣ተመካክረው እንደፈፀሙ አምነው የድርጊቱን አፈፃፀም መርተው አሳይተዋል፡፡ የምርመራ መዝገቡ በተገኘው የተመረዘ ወተትና የአስክሬን ምርመራ፣ በተከሳሾች የእምነት ቃል ተጠናክሮ ለአቃቢ ሕግ ተልኳል፡፡አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ክስ መስርቷል፣ ክሱን ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ሐረርጌ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዳር 12 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ሶስቱም ተከሣሾች እያንዳዳቸው በ13 ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ኢንስፔክተር ስንታየሁ አይደፈር ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል

7 months ago