Logo
SeledaPost
በአስር ዓመት ታዳጊ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት

በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የአስር ዓመት ታዳጊ ናትናኤል ማይክልን በማገት እና በአሰቃቂ ሁኔታ  የገደለው ተከሳሽ ወርቅነህ አሰፋ በሞት እንዲቀጣ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወስኗል።

ተከሳሹ የቀድሞ የመምህርነት ሥራውን ተጠቅሞ ታዳጊውን ናትናኤል ማይክልን ከትምህርት ቤት ሲመለስ ጠልፎ ወደ መኖሪያ ቤቱ ወሰዷል።

ተከሳሹ ልጁን በቦክስ ከመምታት በኋላ በአፍና አፍንጫው ላይ በፕላስተር በማሸግ አፍኖታል። ልጁ ለማምለጥ ሲታገል ተመልሶ በመምጣት በአንሶላ አንቆ ሕይወቱን ካጠፋ በኋላ አስከሬኑን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ ለመሰወር ሞክሯል።

የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539(1)(ሐ) እና 590/2/(ሠ)ን የተላለፈው ተከሳሽ፣ አስቀድሞ በሕፃኑ ቤተሰብ ላይ ገንዘብ የመጠየቅና የራሱን ኑሮ የመቀየር አደገኛ አስተሳሰብ አንግቦ መሆኑ በክሱ ተገልጿል።

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ሕግን ክስና ማስረጃዎች አጥጋቢ ሆኖ በማግኘቱ፣ ተከሳሹ በጭካኔ በተሞላበት መንገድ የፈጸመው አስቦ የመግደልና ታዳጊን የመጥለፍ ወንጀል ተረጋግጦበት፣ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።

Dagu

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.