Logo
SeledaPost
በማርበርግ ቫይረስ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

👉 የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል

ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በሽታው የመያዝ እድላቸውን ለመቀነስ የሚያግዝ Remsedevir የተባለ የፀረ ህዋስ መድኃኒት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የመጀመሪያው የበሽታው ታማሚ ከተገኘበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 17 ድረስ በበሽታው ለተጠረጠሩ ለ73 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። 11 በሚሆኑ ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ መረጋገጡን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል። እነዚህ ታማሚዎች አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ቢሆንም የ6ቱ ህይወት ያለፈ ሲሆን የተቀሩት 5ቱ ደግሞ በህክምና ጣቢያ ወስጥ ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

የበሽታው ምልክቶች ከታየባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 119ኙ የክትትል ጊዜያቸውን ጨርሰው ከለይቶ ማቆያ እንዲወጡ ተደርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ከነበራቸው የማህበረሰብ አካላት ጋር በበሽታው የመያዝ እድላቸውን ለመቀነስ የሚያግዝ Remsedevir የተባለ የፀረ ህዋስ መድኃኒት ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት እስካሁን 16 ለሚሆኑ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ተብለው ለታሰቡ የህክምና ባለሙያዎችን እና ለታማሚዎች ለማድረስ ስለመቻሉ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡via.dagu

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.