ኢትዮጵያ የተቀቀለ የበግና የፍየል ስጋን ወደ ቻይና ልትልክ ነው
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያሏትን ውስን የስጋ ምርት ተቀባይ ሀገራትን ቁጥር ለመጨመር እና ከዘርፋ ያላትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አቅዳ እየሰራች ትገኛለች ሲል የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የማህበራዊ ኢኮኖሚክስና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በአብዛኛዉ የስጋ ምርቷን ጥቂተ በሆኑ የገልፍ ሀገራት ላይ ለሽያጭ ታቀርባለች።
ይህም ሊሆን የቻለዉ የእነዚህን ሀገራት የምርት ጥራትና ደህንነት መስፈርትን ብቻ በማሟላቷ እንደሆነ ተናግረዉ ችግሩን ለመፍታት ሌሎች ሰፋፊ የገበያ መዳረሻዎችን ለማፈላለግ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት ይህን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ሳህሉ በተለይም እንደ ቻይና ወደሚገኙ የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ምርቱን ለመላክ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ከአምናና ካቻምና ጀምሮ የተቀቀለ ስጋን ወደ ቻይና ለመላክ የሚያስችሉ አካሄዶችን በመከተል የተለያዪ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የገለፁት ዶክተር ሳህሉ ይህ ሂደት ከጫፍ መድረሱን አብራርተዋል። በያዝነው ሳምንት የመጨረሻው የፕሮቶኮል ፊርማ ወይንም ስምምነት ከተደረገ በኋላ ምርቶቹን ወደ ቻይና ገበያ መላክ እንደሚቻል ተገልጿል።የተቀቀለ የበግና ፍየል ስጋ ለጊዜው ወደ ቻይና ለመላክ የተፈቀደ ሲሆን አምራቾችንና ላኪዎችን የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡በዘርፋ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በማቀነባበር ሂደት ውስጥ አስፈላጊውን ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ኢንስቲትዮቱ አስታውቋል።dagu
seledadotio

7 months ago