የማርበርግ ቫይረስ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ይቆያል
አንድ ማርበርግ የተያዘ ሰው ከተያዘበት 2ኛ ቀን ጀምሮ አስከ 21 ቀን ባለው ግዜ ውስጥ ምልክት የሚያሳይ ሲሆን በተመሳሳይም ወደሌላ ሰውም ያስተላልፍል። በቫይረስ የሚከሰተው ማርበርግ ከ24 አስከ 88 በመቶ የሞት ምጣኔ እንዳለው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስቴር በማርበርግ በሽታ ዙሪያ በዛሬው እለት ለሚዲያ ባለሙያዎች ስለበሽታው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል።በግንዛቤ ማስጨበጫውም ይህ በቫይረስ የሚከሰተው የማርበርገር ቫይረስ የተያዘ ወንድ ሰው ቢሻለውም በዘር ፈሳሹ ውስጥ ለአንድ አመት ስለሚቆን ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ዶክተር ወልደሰንበት ዋጋነው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
የበሽታው ምልክቶች በአብዛኛው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚታዩ የገለፁት ዶክተር ወልደሰንበት በቫይረሱ የተያዘ ሰው በመጀመሪያዉ ደረጃ ላይ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ ከባድ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ድካም ስሜት እንደሚሰማው ተናግረዋል።ከጥቂት ቀናት በኋላ ከባድ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የደረት እና የጉሮሮ ህመም ስሜቶች የሚሰማ ሲሆን ከ5 እስከ 7 ቀናት ከባድ የደም መፍሰስ ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን እና የቆዳ ስር፣ የጉበት እና የኩላሊት ድካም፣ የንቃተ ህሊና መሳት፣ የብዝሃ-አካል ስራ መቆም እና ሞት ያስከትላል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መቅላት፣ የቆዳ ሽፍታ በተለይ በደረት፣ ጀርባና ሆድ አካባቢ ህመም የሚኖር ይሆናል።ለጊዜው ቫይረሱን የሚያጠፋ የተረጋገጠ ቀጥተኛ መድኃኒት ወይም ክትባት አለመኖሩን የተናገሩት ዶክተር ወልደሰንበት በምርምር ላይ ያሉ የህክምና እና የክትባት አይነቶች እንዳሉ አስረድተዋል።
በህክምና ተቋማት ህክምና የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን ለማስታገስ መሆኑም ተነግራል ፈሳሽ መተካት በከፍተኛ ተቅማጥ እና ማስታወክ የጠፋውን ፈሳሽ መሙላት ያስፈልጋል ተብሏል፤የደም መፍሰስ ቁጥጥር: የደም ግፊትን ማረጋጋት እና የደም መርጋት መከላከል ማከም ያስፈልጋል ተብሏል። የጤና ባለሙያዎች የታመሙ ሰዎችን ሲያክሙ ጓንት፣ ጋውን፣ ጭንብል እና የዓይን መከላከያ የግድ መጠቀም አለባቸው የተባለ ሳሆን ንጽህና እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ ይገባል ተብሏል።
በትላንትናው እለት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በማህበራዊ ትስስር ገፆቸው የ ዕለት የማርበርግ መረጃ ባወጡት መሰረት 2 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በእለቱም 5 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተካሄደ ሲሆን፥ 2 ሰው በቫይረሱ መያዙንና 3 ሰዎች ደግሞ ነጻ መሆናቸው ተገልጿል።በሽታው መከሰቱ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስካሁን 33 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተደረገ ሲሆን ቫይረሱ በ6 ሰዎች ላይ መገኘቱ በላብራቶሪ ተረጋግጧል።
seledadotio

7 months ago