በሞት በህይወት መካከል የነበረን የተጣለ ህፃን ጡቷን በማጥባት ነፍስ የዘራችበት የፖሊስ አባል በደሞዝ ሦስት እርከን እንድታድግና የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላት
#ethiopia | በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ የፖሊስ አባል የሆነች በረሀብ በሞት እና በህይወት መካከል የነበረ የተጣለ ሕፃንን ጡቷን በማጥባት ነብስ የዘራችበት የፖሊስ አባል ሽልማት ተበርክቶላታል።
ዋና ሳጅን ነይማ ጀማል የተባለች የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የቀርሳ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ፅ/ቤት ሃላፊ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጫካ ውስጥ የተጣለ የሶስት ወር ወንድ ልጅ ሕፃን ለተከታታይ ሦስት ቀናት በምግብ እጦት በመቆየቱ በሞትና በሕይወት መካከል ሆኖ ሳለ ጡቷን አጥብታ እንዳተረፈችው ብስራት ሬዲዮ ከዚህ በፊት መዘገቡ ይታወሳል።
የፖሊስ አባሏ ልጅ ከወለደች ገና የስድስት ወር አራስ የነበረች ሲሆን በሰብዓዊነት ጡቷን ለአንድ ሰዓት ያህል አጥብታ የተዳከመውን ህፃን ነብስ የዘራችበት በመሆኑ ለአደረገች ሰብዓዊነት የተሞላበት ድርጊት ሽልማት ተበርክቶላታል።
ለፖሊስ አባሏ ሽልማቱ የተበረከተላት የነጭ ሪቫን ቀን አስመልክቶ ሲሆን የስንቄ ባንክ የፖሊስ አባልዋ ላበረከተችው ድንቅ የሰብዓዊነት ተግባር ለመጀመርያ ግዜ የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ እንዳበረከተላት የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ ገልጿል።
የዋና መምርያው ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ናስር መሃመድ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት የፖሊስ በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል የሚለውን መርህ ያንፀባረቀው የዋና ሣጅን ነይማ ጀማል ተግባር የክልሉን የፖሊስ አርማ ከፍ ያደረገ እና ያኮራ ተግባር በመሆኑ ካለችበት የደሞዝ እርከን በሶስት እርከን እንድታድግ የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምርያ እንደፈቀደ ተናግረዋል።
የፖሊስ አባሏ ተግባር በኩሪ ገድል ታሪክ ላይ የሚመዘገብ መሆኑን የተናገሩት ረዳት ኮሚሽነር ናስር መሀመድ በቀጣይም በሴቶች እና ህጻናት ዙርያ የሚሰሩ ተግባራት ላይ አጠንክሮ ለመስራት እንደማሳያ እንደሚሆንም ገልፀዋል።
በዋና ሳጅን ነይማ ጀማል የጡት ወተት በህይወት የተረፈዉ የሶስት ወር ህፃን አሁን ላይ በፍጹም ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ታውቋል ያለው ዳጉ ጆርናል ነው።

7 months ago