Logo
FIDEL POST NEWS
በሞት  በህይወት መካከል የነበረን የተጣለ ህፃን ጡቷን በማጥባት ነብስ የዘራችበት የፖሊስ አባል በደሞዝ ሶስት እርከን እንድታድግና የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላት

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ የፖሊስ አባል የሆነች  በረሀብ በሞት እና በህይወት መካከል የነበረ የተጣለ ሕፃንን ጡቷን በማጥባት ነብስ የዘራችበት የፖሊስ አባል ሽልማት ተበርክቶላታል።ዋና ሳጅን ነይማ ጀማል  የተባለች የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የቀርሳ ወረዳ  ፖሊስ ፅ/ቤት የሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ፅ/ቤት ሃላፊ  ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጫካ ውስጥ የተጣለ የሶስት ወር ወንድ ልጅ  ሕፃን   ለተከታታይ ሶስት ቀናት በምግብ እጦት  በመቆየቱ በሞትና በሕይወት መካከል ሆኖ ሳለ ጡቷን አጥብታ እንዳተረፈችው መዘገቡ ይታወሳል።

የፖሊስ አባሏ ልጅ ከወለደች ገና የስድስት ወር አራስ የነበረች ሲሆን በሰብዓዊነት ጡቷን ለአንድ ሰዓት ያህል አጥብታ የተዳከመውን ህፃን ነብስ የዘራችበት በመሆኑ ለአደረገች  ሰብዓዊነት የተሞላበት ድርጊት ሽልማት ተበርክቶላታል።ለፖሊስ አባሏ ሽልማቱ የተበረከተላት የነጭ ሪቫን ቀን አስመልክቶ ሲሆን የስንቄ ባንክ የፖሊስ አባልዋ ላበረከተችው ድንቅ የሰብዓዊነት ተግባር ለመጀመርያ ግዜ የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ እንዳበረከተላት የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ ገልጿል።

የዋና መምርያው ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ናስር መሃመድ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት የፖሊስ በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል የሚለውን መርህ ያንፀባረቀው የዋና ሣጅን ነይማ ጀማል ተግባር  የክልሉን የፖሊስ አርማ ከፍ ያደረገ እና ያኮራ ተግባር በመሆኑ ካለችበት የደሞዝ እርከን በሶስት እርከን እንድታድግ የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምርያ እንደፈቀደ ተናግረዋል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.